1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ሰኞ፣ ጥቅምት 28 2009

የኢትዮጵያ መንግስት ለስድስት ወር የሚቆየዉን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከደነገገ ዛሬ አንድ ወር ደፈነ። በዚህ ጊዜ ዉስጥ የመንግስት ፀጥታ ኃይላት በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ስለማሰራቸዉ ፣ ሰዎችም ስለ መሞታቸው ሲዘገብ ቆይቷል።

https://p.dw.com/p/2SIRv
Ethiopia State of Emergency Merkel (picture alliance / AP Photo)
ምስል picture-alliance/AP Photo

MMT_SoE in a Course of One Month - MP3-Stereo

መንግስትን ጨምሮ ሌሎች የህብረተሰቡ ክፍሎችም አዋጁ ሰላምና መረጋጋት ማምጣቱን ቢናገሩም ሌሎች ደግሞ በቤት ፍተሻ ስም የፀጥታ አካላት «በስርቆት» መሳተፈቸዉንና የግለሰቦችን መብቶች መጣሳቸውን ይናገራሉ።

የአዋጅ አፈፃጸም አሳድሯል ስለሚባለው ተጽእኖ የተለያዩ ሰዎችን አነጋግረን ነበር። የሰበታ ነዋሪ ነኝ የሚሉት አቶ ዩሱፍ ኑሪዬ አዋጁ ሳይታወጅ በፊት ከተማዋ «በፍርሃት ተዉጣ ነበረ፣ አብዛኛዉ ስራም ቆሞ ነበር» ሲሉ ለዶቼ ቬሌ ይናገራሉ። ከአዋጁ ከታወጀ በኋላ ግን ይህ ተለውጧል ይላሉ። 

ስማቸዉ እንዳይጠቀስ የፈለጉት እኚህ የባህርዳር ነዋሪ ደግሞ የአዋጁ አፈፃጸም በከተማዋና አካባቢው የተለያዩ ተጽእኖዎች ማሳደሩን ነው የሚናገሩት።

ስማቸዉ እንዳይጠቀሰ የጠየቁት የአዳማ ነዋሪ ካዩት እና ከሰሙት፣ አዋጁ ሥራ ላይ የዋለበት ያለፈው አንድ ወር « በአገሪቷ የከፋ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የተፈፀመበት ወር ነበረ ይላሉ። ለዚህም ምክንያት የሚሉትን ተናግረዋል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን አፈፃፀም ለመመርመር የተቋቋመዉ «አጣሪ ቦርድ» በቀናት ውስጥ የአፈጻጸሙ ዘገባ ይፋ ይደረጋል ብሎ እንደሚጠበቅ የቦርዱ ሊቀመንበር አቶ ታደሰ ሆርዶፋ ለዶቼ ቬሌ ተናግረዋል። ቦርዱ  ዘገባውን የሚያወጣው የታሳሪዎችንና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ጉዳይ በተመለከተ የደረሱትን መረጃዎች መርምሮ መሆኑን አቶ ታደሰ ገልፀዋል። 

በሚቀጥሉት ቀናት ዉስጥ ይፋ ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀው ይህ ዘገባ  «ማን በምን ምክንያት   በቁጥጥር ስር እንደዋለ፣ የት እንደታሰረ  ግልፅ ያደርጋል» ይላሉ አቶ ታደሰ።

በዚህ ጉዳይ በፌስቡክ ገፃችን ተከታዮቻችንን አወያያትን ነበር። አስተያየት ከሰጡን ዉስጥም «አዋጁ ተመችቶኛል፣ ሰላምና ልማታችን ይቀጥላል፣ በርካታ ሰዎች መታሰራቸው ብቻ አይደለም መታየት ያለበት፣ ምን ስለሰሩ የሚለው ጉዳይ አብሮ መታየት አለበት» ያሉ ይገኑኙበታል ። «አዋጁን አወጡት ያሏቸውንና ከኢትዮጵያ መንግስት ጀርባ ሆነው የሚያሾሩት ሲሉ የገለጹዋቸውን» ግለሰቦች የዘረዘሩ በሌላ በኩል ደግሞ «አፋችን ተዘግትዋል፣ ሰዉ ታስራል፣ ተገድሏል» የሚሉ አስተያየቶችም ደርሰውናል። 

መርጋ ዮናስ

ኂሩት መለሰ