1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሽከርካሪዎች ብሶትና የመንግሥት ምላሽ፣

ሰኞ፣ ሐምሌ 23 2004

በእጅ ስልክ የአጫጭር የጽሑፍ መልእክት ማስተላለፊያ መሥመራችን በኩል ፣ ምሬታቸውንም ሆነ ብሶታቸውን የሚገልጹ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች ሾፌሮች ፤ በቃል የሚነገረውና በተግባር የሚተረጎመው ሰፊ ልዩነት አለው ። በቦታ መጨናነቅ ፣ በማረፊያና

https://p.dw.com/p/15gpj
Using a combination of manpower and machinery, workers at Djibouti port unload 20,000 tons of wheat, Aug. 16, 2000. The port on the Gulf of Aden has seen a dramatic increase in business during the last two years, mainly to and from landlocked Ethiopia. Its management has been signed over to Dubai Ports International for the next 20 years, to improve its efficiency. (AP Photo/Sayyid Azim)
ምስል AP

መጸዳጃ ቦታ ችግር፤ ገንዘብ የሚመነዘርበት ሥፍራ ባካባቢው አለመኖር ፣ በእነዚህና በመሳሰሉ ችግሮች እየተሠቃየን ነው፤ ነው የሚሉት። በተለይ፤ ቡናም ሆነ ሌሎች ምርቶችን ጭነው ጂቡቲ የሚያራግፉና ፤ ብረታ ብረትና የተለያዩ ሸቀጣ ሸቀጦችን ይዘው የሚመለሱ አሽከርካሪዎች ፣ ሥራው እንደሚባለው በቅልጥፋና አይካሄድም፣ በመሃሉም ፣ ለተለያዩ ከባድ ችግሮች እንዳረጋለን ሲሉ ፣ ችግራቸውን መንግሥት ያቃልላቸው ብሎም ዘላቂ መፍትኄ ያስገኝ ዘንድ ይጠይቃሉ። ወደ ጂቡቲ የሚመላለሱትን ሾፌሮች ጉዳይ በተመለከተ ተክሌ የኋላ አንድ ዘገባ አለው።

በተናጠልና በኅብረት ወደዚህ በSMS የሚጸፉ ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች ሾፌሮች ቁጥር የጨመረ ይመስላል። ስልካቸውንም እየጻፉ ደውላችሁ ልታነጋግሩን ትችላላችሁ በማለታቸው ፤ ብሶታቸው በእርግጥ ምን እንደሆነ ለመገንዘብ፤ ወደ አንደኛው አሽከርካሪ ደወልሁና ፣ ስለሁኔታው እንዲያብራሩልን ጠይቄአቸው ሲመልሱ--

የእነዚህን ወገኞች ችግር ከዚያው ካፍንጫው ሥር በማየት ተገቢውን ምላሽም ሆነ መፍትኄ መስጠት አይሳነውም ብዬ በማሰብ ፣ ጂቡቲ ወደሚገኘው ኤምባሲ ፣ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በተደጋጋሚ ስደውል ብቆይም ለቃለ ምልልስ ዝግጁ የሚሆን ሰው በማጣቴ ወደ ዋናው የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መ/ቤት ደወልሁ። የነዚህን ሾፌሮች ችግር ለመቅረፍ ብሎም ለመፍታት መላው ምንድን ነው? ፣ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ የሆኑትን አምባሳደር ዲና ሙፍቲን ጠየቅሁ።

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሠ