1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአባይ ተፋሰስና የኢትዮጵያ አቋም

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 13 2002

የአባይ ተፋሰስ አባል አገራት የትብብር መድረክ በዉሃዉ ፍትሃዊ ክፍፍል ላይ ያዘጋጀዉን ሰነድ ግብፅ፤ ሱዳንና ኤርትራ አልፈርምም ማለታቸዉን የኢትዮጵያ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አስታዉቋል።

https://p.dw.com/p/N21S
አወዛጋቢዉ የአባይ ወንዝ ፏፏቴምስል picture-alliance / dpa

ፅህፈት ቤቱ ትናንት ለዓለም ዓቀፍ የመገናኛ ብዙሃን ዘጋቢዎች በሰጠዉ መግለጫም ኤርትራን ጨምሮ ግብፅና ሱዳን ስምምነቱን ባይፈርሙም የፊታችን የአዉሮጳዉያኑ ግንቦት 14 2010ዓ,ም በቀሪዎቹ የተፋሰሱ ስምንት አባል አገራት ስምምነቱ እንደሚፈፀም ገልጿል። የግብፅ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ በሰጠዉ መግለጫ ስምምነቱ የአገሪቱን ብሄራዊ ደህንነት እንደሚጋፋ፤ ግብፅም የህልዉናዋ ጉዳይ የሆነዉንና በናይል ዉሃ የሚደረግን የተናጠል ስምምነት ዝም ብላ አትመለከትም ብሏል።

ታደሰ እንግዳዉ/ሸዋዬ ለገሰ

አርያም ተክሌ