1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአባይ ተፋሰስ አገሮች የውሃ አጠቃቀም ችግር

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 14 2002

የአባይ ወንዝ ተፋሰስ ሃገራት የውሃውን ክፍፍል ፍትሃዊ የሚያደርግ አዲስ ውል ለማስፈን ያደረጉት ሙከራ በግብጽ ግትርነት የተነሣ ገቢር ሣይሆን ቀርቷል። ግብጽ ከእንግሊዝ ጋር እ.ጎ.አ. በ 1929 ዓ,ም. አድርጋ በነበረው የቅዥ አገዛዝ ዘመን ስምምነት ባገኘችው ሰፊ ድርሻና የበላይነት ለመቀጠል ነው የምትፈልገው።

https://p.dw.com/p/N35M
ምስል picture-alliance/dpa

በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ግብጽ ሃብቱን እኩል ለመካፈል እንዳይቻል ስምምነቱን እያስተጓጎለች ነው በማለት ስትወቅስ ከተቀሩት ስድሥት የተፋሰሱ ሃገራት ጋር አዲሱን ውል እንደምታሰፍን ሰሞኑን አስታውቋለች። ጉዳዩ በአካባቢው ,ለተጨማሪ ውጥረት ምክንያት እንዳይሆን በጣሙን ያሰጋል። አዜብ ታደሰ በጉዳዩ የዓለምአቀፉን ውዝግብ ተመልካች ቡድን የአፍሪቃ ተጠሪ ኤጀይ ሆግንዶርንን አነጋግራ ያጠናቀረችው ዘገባ የሚከተለው ነው።

አዜብ ታደሰ፣

አርያም ተክሌ