የአባይ ግድብ አጥኚዎች መመረጣቸው
ዓርብ፣ ሚያዝያ 2 2007ማስታወቂያ
ታላቁ የአባይ ግድብ በታችኛዎቹ የተፋሰሱ ሃገራት ላይ ሊያስከትል የሚችለውን የተለያዩ ተፅእኖዎች የሚያጠኑ 2 ኩባንያዎች መመረጣቸውን የኢትዮጵያ የውሐ መስኖና የኃይል ሚኒስቴር አስታወቀ ።አጥኚዎቹ ኩባንያዎች የተመረጡት የኢትዮጵያ የግብፅና የሱዳን የወሃ ሃብት ሚኒስትሮች የሚገኙበት የቴክኒክ ኮሚቴ አዲስ አበባ ውስጥ ለሁለት ቀናት ባካሄደው ስብሰባ ላይ ነው ።የኩባንያዎቹ ማንነት ግን አልተገለፀም ። የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ባለሥልጣን ለ,ዶቼቬለ እንደተናገሩት የኩባንያዎቹ ስም ወደ ፊት ይገለፃል ። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝርዝር ዘገባ አለው ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሄር
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ