1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአባይ ግድብ፤ ኢትዮጵያና ግብፅ

ዓርብ፣ ሐምሌ 11 2006

ካርቱም-ሱዳን ይደረግ የነበረዉ የሠወስትዮሾ ድርድር የተቋረጠዉ ኢትዮጵያና ግብፅ ባለመግባባታቸዉ ነበር።አሁን ግን የሁለቱ ሐገራት መሪዎች ባለፈዉ ወር ማላቦ-ኢኳቶሪያል ጊኒ ባደረጉት ዉይይት ድርድሩ እንዲቀጥል ተስማምተዋል

https://p.dw.com/p/1CfCo
ምስል William Lloyd-George/AFP/Getty Images

ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ የምታስገነባዉ ግዙፍ ግድብ በዉሐዉ ፍሰት ላይ ሥለሚያደርሰዉ ተፅዕኖ የኢትዮጵያ፤ የሱዳንንና የግብፅ ባለሥልጣናት የሚያድርጉት ዉይይት እንዲቀጥል ኢትዮጵያና ግብፅ ተስማሙ።ካርቱም-ሱዳን ይደረግ የነበረዉ የሠወስትዮሾ ድርድር የተቋረጠዉ ኢትዮጵያና ግብፅ ባለመግባባታቸዉ ነበር።አሁን ግን የሁለቱ ሐገራት መሪዎች ባለፈዉ ወር ማላቦ-ኢኳቶሪያል ጊኒ ባደረጉት ዉይይት ድርድሩ እንዲቀጥል ተስማምተዋል።ከሥድስት ወር በፊት የተቋረጠዉ ድርድር የሚቀጥልበት ሥፍራና ጊዜ ግን በገለፅ አልተነገረም።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ