1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአባይ ግድብ ውዝግብና ስምምነት

እሑድ፣ መጋቢት 27 2007

አንዳንድ የመስኩ ባለሞያዎች በስምምነቱ ኢትዮጵያ ኃይል ከማመንጨት በተጨማሪ በሌሎችም መስኮች ከግድቡ ተጠቃሚ ልትሆን የምትችልበትን እድል አልተጠቀመችም ሲሉ ይተቻሉ ። መንግሥት በበኩሉ ስምምነቱ ብሔራዊ ጥቅም ከማስጠበቅ ወደ ኋላ የሚል አይደለም በማለት ይከራከራል ።

https://p.dw.com/p/1F2XO
Ägypten Äthiopien Damm am Nil
ምስል William Lloyd-George/AFP/Getty Images

የኢትዮጵያ የግብፅና የሱዳን መሪዎች ስለ ታላቁ የአባይ ግድብ በቅርቡ የተፈራረሙት ስምምነት እስካሁን በመካከላቸው ሰፍኖ የቆየውን ጥርጣሬ የማስወገድና ከአባይ ውኃ አጠቃቀም ጋር የተያያዙ ሌሎች ችግሮችን ደረጃ በደረጃ የማቃለል ተስፋ ተጥሎበታል ። የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ መርሆዎች መግለጫ Declaration of Principles on Ethiopian Renaissance Dam የተባለው ይኽው ስምምነት በበጎ እርምጃነቱ ቢወደስም ልዩ ልዩ ጥያቄዎችንም ማስነሳቱ አልቀረም ። አንዳንድ የመስኩ ባለሞያዎች በስምምነቱ ኢትዮጵያ ኃይል ከማመንጨት በተጨማሪ በሌሎችም መስኮች ከግድቡ ተጠቃሚ ልትሆን የምትችልበትን እድል አልተጠቀመችም ሲሉ ይተቻሉ ። መንግሥት በበኩሉ ስምምነቱ ብሔራዊ ጥቅም ከማስጠበቅ ወደ ኋላ የሚል አይደለም በማለት ይከራከራል ። በመጪው እሁድ የሚተላለፈው እንወያይ የአባይ ግድብ ውዝግብና ስምምነት በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ነው ።

ኂሩት መለሰ

ልደት አበበ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ