1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአብርሃም አስመላሽ ዜና እረፍት

ዓርብ፣ ጥቅምት 22 2006

በበርካታ አዝናኛ መነባንቦቹ የሚታወቀው ኢትዮጵያዊው አርቲስት አብርሃም አስመላሽ አረፈ ። አርቲስት አብርሃም ላለፉት 3 ወራት በኑርንበርግ ጀርመን በህክምና ሲረዳ ነበር ።

https://p.dw.com/p/1AANl
ምስል Fotolia/ stokkete

አርቲስት አብርሃም አስመላሽ ለበርካታ ዓመታት በኢትዮጵያ ራድዮ የቅዳሜ መዝናኛ ዝግጅት ልዩ ልዩ ማህበራዊ ጉዳዮችን አዋዝቶ በሚያቀርብበት ተወዳጅ መነባንቦቹና ጭውውቶቹ ይታወቃል ። አዲስ አበባ በልማዱ ፈረንሳይ ለጋስዮን ተወልዶ ያደገው አብርሐም በአካባቢው ለንግድ ከሚመጡ የመንዝና የወሎ ነጋዴዎች በቀሰመው የአነጋገር ዘይቤ የሚያቀርባቸው መነባንቦች የልዩ ተስጥኦው ቋሚ ምስክሮች ናቸው ። አብርሐም ለህትመት ያልበቁ በርካታ ስራዎችም ነበሩት ። ለቤተሰቦቹ ለወዳጅ ዘመዶቹና ለስራዎቹ አፍቃሪዎች ዶቼቬለ የአማርኛው ክፍል መፅናናትን ይመኛል ። እዚህ ጀርመን መጥቶ እንዲታከም እርዳታ ያስተባበሩለት የኢትዮጵያ አርቲስቶች ማህበር የጀርመን ተጠሪ አቶ ተፈሪ ፈቃደ የአብርሃምን አስከሬን ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ የበጎ ፈቃደኖችን አስቸኳይ እርዳታ ጠይቀዋል ። አቶ ተፈሪን በስልክ አነጋግረቸዋል ።

ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ