የተመድ ዋና ጸሀፊ አስተያየት
ማክሰኞ፣ የካቲት 20 2010ማስታወቂያ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ሥልጣን ለመልቀቅ ያሳለፉትን ውሳኔ በበጎ መቀበሉን አስታወቀ። የድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶንዮ ጉተሬሽ የአቶ ኃይለ ማርያም ውሳኔ በሀገሪቱ የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት እድል የሚሰጥ እርምጃ ነው ብለዋል። ድርጅቱ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሥልጣን መልቀቅ ጥያቄ ላይ አስተያየት መስጠቱ እንዴት ይታያል ሲል ዶቼቬለ የጠየቃቸው አንድ የፖለቲካ ተንታኝ ድርጅቱ አስተያየት የሰጠው የኢትዮጵያ ጉዳይ አሳሳቢ ደረጃ ላይ በመድረሱ ነው ሲሉ በተመድ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ፅህፈት ቤት ቃል አቀባይ ደግሞ ድርጅቱ አስተያየት መስጠቱ አዲስ ነገር አይደለም ብለዋል። መክብብ ሸዋ ከዋሽንግተን ዲሲ ዝርዝር ዘገባ አለው።
መክብብ ሸዋ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ