1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአንዋር መስጊድ ተቃዉሞ

ሰኞ፣ ሐምሌ 14 2006

ሐምሌ 11፤ አርብ አዲስ አበባ አንዋር መስጊድ በተቀሰቀሰ ከፍተኛ ግጭት በርካታ ሰዎች መጎዳታቸዉ ተሰምቶአል። ተሰምቶአል። የአይን እማኞች ፖሊሶች እና የጸጥታ ኃይላት ናቸዉ ያሏቸዉ፤ በታላቁ አንዋር መስጊድ ለጁምዓ ሶላት የተሰበሰበዉን ምዕመን በያዙት ዱላ መደብደባቸዉንና ወንድ ሴት ሳይለዩ እያጋዙ መዉሰዳቸዉን ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል።

https://p.dw.com/p/1CgGA
Addis Abeba
ምስል picture alliance / landov

በሌላ በኩል የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነች ወጣት በአንዋር መስኪድ አከባቢ በተፈጠረው ረብሻ በፖሲሶች ተይዛ ከባድ ድብደባ እንደተፈጸመባት የፓርቲዉ ሊቀመንበር ለዶቼ ቬለ ገልፀዋል። ስለዚሁ ጉዳይ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለስልጣናትን አስተያየት ያደረግነዉ ተደጋጋሚ ጥረት አልተሳካም።
«የታሰሩ የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊዎች ይፈቱ» በሚል አንዋር መስጊድ በተነሳ ተቃዉሞ በርካታ ፖሊሶች ምዕመኑን በዱላ በመደብደብ ለመበተን ሲሞክሩ በርካታ ግርግርና ረብሻ እንዲሁም የተኩስ ድምፅ መሰማቱን አቶ ሃምዛ ጀፈር እንዲህ ገልፀዉልናል። አቶ ሃምዛ ከመስጊድ ከሌሎች ጋር ታፍሰዉ ተወስደዉ መደብደባቸዉና መሰቃየታቸዉን፤ ከዝያም ከለሊቱ ስምንት ሰዓት ተኩል ላይ መለቀቃቸዉን ተናግረዋል። ለጁማ ፀሎት ወደ አንዋር መስጊድ ሄጄ ነበር ነገር ግን ረብሻ ላይ ነበር የደረስኩት ያሉት ወ/ሮ ሃያት በበኩላቸዉ፤ በፖሊሶች ተይዘዉ ተወስደዉ እንደነበር ገልፀዋል።
በአንዋር መስኪድ አከባቢ ረብሻ ሲቀሰቀስ አካባቢዉ ላይ የነበረችዉ የሰማያዊ ፓርቲ አባል ወጣት ወይንሸት ሞላ፤ በፖሊሶች ድብደባ ተፈፅሞባት መጎዳትዋንና አሁንም በእስር ቤት እስዋን መጠየቅ እንዳልተቻለ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ይልቃል ጌትነት ተናግረዋል። ስለዚሁ ጉዳይ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለስልጣናትን አስተያየት ያደረግነዉ ተደጋጋሚ ጥረት አልተሳካም። «የታሰሩት የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ይፈቱ» በሚል በተለያዩ ግዝያት ተቃዉሞዉ መቀጠሉ ይታወቃል።

አዜብ ታደሰ
ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ