1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«አንዳርጋቸው ጽጌ ይፈታ»

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 30 2010

በ2006 ዓ.ም. የመን ውስጥ ተጠልፈው ኢትዮጵያ በእስር ላይ የሚገኙት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲፈቱ የሚጠይቅ የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ዘመቻ ትናንት ተጀምሯል። «አንዳርጋቸው ጽጌ ይፈታ» በሚል መሪ ቃል የተጀመረው ዘመቻ እስከ ነገ ረቡዕ በአጠቃላይ ለሦስት ቀናት እንደሚቆይ ተነግሯል።

https://p.dw.com/p/2xN7Q
Jemen Sanaa Flughafen
ምስል picture-alliance/dpa/Y. Arhab

የመን የሚገኘው ሰንዓ አየር ማረፊያ

በ2006 ዓም የመን ውስጥ ተጠልፈው ኢትዮጵያ በእስር ላይ የሚገኙት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲፈቱ የሚጠይቅ የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ዘመቻ ትናንት ተጀምሯል። «አንዳርጋቸው ጽጌ ይፈታ» በሚል መሪ ቃል የተጀመረው ዘመቻ እስከ ነገ ረቡዕ በአጠቃላይ ለሦስት ቀናት የሚቆይ መኾኑን በግለሰብ ደረጃ ተናሳስተው ሐሳቡን እያንሸራሸሩ የሚገኙት አስተባባሪዎቹ ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል። አቶ አንዳርጋቸው የመን ውስጥ ተይዘው ወደ ኢትዮጵያ ተላልፈው ከተሰጡበት ጊዜ አንስቶ የት እስር ቤት እና በምን አይነት ኹኔታ ውስጥ እንደሚገኙ በውል አይታወቅም። አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲፈቱ በማኅበራዊ መገናኛ አውታሮች ጥሪ ያስተላለፉትን አስተባባሪዎች በማነጋገር የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር 
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሰ