የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ ወቀሳ

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) ትናንት በአዲስ አበባ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ጠርቶ የነበረ ሲሆን፣ የፓርቲው አባላት እና ደጋፊዎች ሰልፍ ለመዉጣት በዝግጅት ላይ እንደነበሩ በፌዴራል ፖሊስ የኃይል ተግባር

እንደተፈፀመባቸው የፓርቲው ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት አቶ ተክሌ በቀለ ለዶይቸ ቬለ ገለጹ። አንድነት በአባላቱ ላይ ተፈፀመ ስላለው ድብደባ ደረሰ ስላለው ጉዳት ከመንግሥት ጽሕፈት ቤት እና ከአዲስ አበባ መስተዳድር አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ የሚመለከታቸው ባለሥልጣናት ስብሰባ ላይ ናቸው በመባሉ ሳይካሳ ቀርቶዋል።

አርያም ተክሌ

ነጋሽ መሀመድ

ተከታተሉን