1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአንድነት መግለጫ

ዓርብ፣ ግንቦት 28 2007

አቶ ትዕግስቱ ስለ ምርጫው በሰጡት አስተያየት ፓርቲያቸው በቅስቀሳ ወቅት ያቀረባቸው ሃሳቦች ሙሉ በሙሉ ለህዝቡ ባለመቅረባቸው የፓርቲውን አቋም ለህዝቡ በትክክል ማሳወቅ አለመቻላቸውን አስታውቀዋል ።

https://p.dw.com/p/1Fbqr
Addis Ababa (Äthiopien)
ምስል picture alliance/landov

[No title]

የአንድነት መግለጫ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እውቅና የሰጠው በአቶ ትዕግስቱ አወል የሚመራው አንድነት ለዴሞክራሲና ፍትህ ፓርቲ የምርጫውን ውጤት መቀበል ተገቢ ነው ብሎ እንደሚያምን አስታወቀ ።አቶ ትዕግስቱ አወል ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ፓርቲያቸው ይህን የሚለው መራጩን ህዝብ በማክበር መሆኑን ተናግረዋል ። ሆኖም አቶ ትዕግስቱ ስለ ምርጫው በሰጡት አስተያየት ፓርቲያቸው በቅስቀሳ ወቅት ያቀረባቸው ሃሳቦች ሙሉ በሙሉ ለህዝቡ ባለመቅረባቸው የፓርቲውን አቋም ለህዝቡ በትክክል ማሳወቅ አለመቻላቸውን አስታውቀዋል ። በአፋርና በአዋሳም ታዛቢዎቻቸው እስር ና ድብደባን ጨምሮ ልዩ ልዩ ወከባዎች እንደተፈፀሙባቸውም አስረድተዋል ።ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝር ዘገባ አለው

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሰ