1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአንድነት አመራር አባላት ጊዜያዊ እገታ

ዓርብ፣ መስከረም 17 2006

የኣንድነት ለዲሞክራሲ እና ፍትህ ዓመራር አባላት የፊታችን እሁድ አዲስ ኣበባ ላይ ለጠሩት ሰልፍ ቅስቀሳ ለማድረግ እንዳልቻሉ ኣስታወቁ በኢትዮጵያ ፓርላማ ብቸናው የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ የሆኑትን አቶ ግርማ ሰይፉን ጨምሮ የፓርቲው ዓመራሮች ዛሬ ለተወሰኑ ሳዓታት በፓሊሶች ታግተው መለቀቃቸውን ፓርቲው ኣስታውቋል ።

https://p.dw.com/p/19pg5
ምስል Solomon Mengist

የፓርቲው ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ ዲዳዳም ከትናንት በስቲያ በተመሳሳይ ሁኔታ ታግተው መለቀቃቸው ይታወሳል በኢትዮጵያ ፓርላማ ብቸናው የተቃዋሚ ፓርቲ ተወካይ እና የኣንድነት ለዲሞክራሲ እና ፍትህ ፓርቲ ከፍተና ዓመራር አቶ ግርማ ሰይፉ ዛሬ ከታገቱበት የአራዳ ክ/ከተማ ፓሊሲ መምርያ ሆነው በእልክ ለዶቸቤሌ እንደገለጹት እሳቸውን ጨምሮ ኣጠቃላይ የፓርቲው ዓመራሮች እና ለቅስቀሳየተሰማሩ አባላቱ ባይታሰሩም በእሳቸው ኣባባል ታግተዋል አቶ ግርማ እንደሚሉት በኣሰራር ሰላማዊ ሰልፉ ተከልክለዋል በሰበብ ኣስባቡ ሌላ ጊዜ ሌላ ቦታ እየተባለ ግን ይነገራቸዋል ምክኒያታቸው ደግሞ የቅስቀሳ ፈቃድ የላችሁም የሚል ነው የቅስቀሳ ፈቃድ በራሱ ህገ ወጥ ነው ያሉት አቶ ግርማ ሰይፉ ፈቃዱንም ለማምጣት ፈቃድ ሰጪውም ሆነ የሚሰጥበት ቦታም ኣይታወቅም ብለዋል።

Äthiopien Partei UDJ
ምስል DW/Y.Gebreegziabher

ይሁን እንጂ ፖሊስ የቅስቀሳ ቡድኑንም ሆነ የፓርቲውን ዓመራሮች ከማዋከብ ኣልታቀበም ያለመያዝ መብት ያላቸው አቶ ግርማ ሰይፉም ጭምር ከእገታውኣላመለጡም አቶ ግርማ እንደሚሉት ኣሁን የተያዘው ነገር እገታ ነው እሰሩን ብንልም ፈቃደና ኣይደሉም የሚሉት አቶ ግርማ ለጊዜው ቡድኑን በማገት እንቅስቃሴውን ማስተጎጎል ነው የተፈለገው ብለዋል ። በኣጠቃላይ ይላሉ አቶ ግርማ ሰይፉ የዚህ ዓይነቱ ኣሰራር በሰላማዊ መንገድ ለሚንቀሳቀሱት ኃይሎች በር እየዘጋ በህገ ወጥ መንገድ ለመታገል ለመረጡ ቡድኖች ጥርጊያ መንገድ ማመቻቸት ነውድምጽ አምስት አቶ ግርማ ሰይፉ በአቶ ግርማ ሰይፉ መግለጫ መሰረት ዛሬ ከቀትር በኃላ በሶስት ተሽከርካሪዎች አማካይነት የተሰማራው የቅስቀሳ ቡድን ታግቶ ቅስቀሳውም ተጨናግፈዋል ዓላማውም ሰላማዊ ሰልፉን ማሰናከል ነው ያሉት አቶ ግርማ ሰልፉን በተመለከተ ኣመራሩ ተሰብስቦ ፖለቲካዊ ውሳኔ እንደሚሰጥ ኣስታውቀዋል ይህንኑ ኣስመልክተው የበኩላቸውን ምላሽ እንዲሰጡን የኣራዳ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያን በስልክ ለማነጋገር ያደረግነው ተደጋጋሚ ሙከራ ኣልተሳካም

ጃፈር አሊ
ሂሩት መለሰ


ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ