1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአንጌላ ሜርክል በፈረንሳይ የመጨረሻ ይፋዊ ጉብኝት  

ዓርብ፣ መስከረም 7 2014

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኤማኑኤል ማክሮ ከስልጣናቸዉ ለመሰናበት ጥቂት ጊዜያት የሚቀራቸዉን የጀርመንዋን መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክልን ትናንት ምሽት በኤሊዜ ቤተ መንግሥት ደማቅ አቀባበል አደረጉላቸዉ። ፕሬዚዳንት ማክሮ እና መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል በዓለም አአፍ እና አዉሮጳ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

https://p.dw.com/p/40Scn
Paris Kanzlerin Merkel und Präsident Macron
ምስል Jonathan Rebboah/PanoramiC/imago images

በዓለም አቀፍ እና አዉሮጳ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል

የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኤማኑኤል ማክሮ ከስልጣናቸዉ ለመሰናበት ጥቂት ጊዜያት የሚቀራቸዉን የጀርመንዋን መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክልን ትናንት ምሽት በኤሊዜ ቤተ መንግሥት ደማቅ አቀባበል አደረጉላቸዉ። ፕሬዚዳንት ማክሮ እና መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል በዓለም አቀፍ እና አዉሮጳ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል። የትናንቱ የሊዜ ቤተ-መንግሥት ስነ-ሥርዓት በፈረንሳይ የሜርክል የመጨረሻ አቀባበል ተብሎለታል። የፊታችን መስከረም 16 በጀርመን ምርጫ እስኪካሄድ እና ቀጣዩ የመንግሥት መሪ ፓርቲ እስኪታወቅ የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኤማኑኤል ማክሮ እና መራሂተ መንግሥት በፍራንኮ-ጀርመን ግንኙነት እጅ ለእጅ ተያይዘዉ ስራቸዉን በትብብር እንደሚቀጥሉ ተገልፆአል። ሁለቱ መሪዎች ትናንት ምሽት በአፍጋኒስታን ቀዉስ፤ በሊቢያ፤ በኢራን እና በዩክሬይን ጉዳዮች ዙርያ በዋና አጀንዳነት አንስተዉ መነጋገራቸዉ ተመልክቶዋል። በሌላ በኩል የአዉሮጳ ዋና ዋና ተግዳሮቶች በተባሉት፤ በመከላከያ ጉዳዮች፤ በስደተኞች እና ተገን ጠያቂዎች እንዲሁም በዲጂታል መረጃ ልዉዉጥ ላይ ሁለቱ መሪዎች የመከሩባቸዉ ጉዳዮች መሆናቸዉም ተመልክቶአል። 

ሃይማኖት ጥሩነህ
አዜብ ታደሰ 
እሸቴ በቀለ