1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአንጌላ ሜርክል የቱርክ ጉብኝት

ማክሰኞ፣ መጋቢት 21 2002

የጀርመኗ መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ቱርክን በመጎብኘት ላይ ናቸው ። ሜርክል ወደ ቱርክ ከመጓዛቸዉ በፊት በመገናኛ ብዙሃን ለህዝባቸዉ ባድርጉት ሳምንታዊ ንግግር ላይ በጀርመን የሚኖሩ የቱርክ ተወላጆች የጀርመንኛ ቋንቋን እና የአገሪቷን ባህል ጠንቅቀዉ አዉቀዉ ተዋህደዉ እንዲኖሩ ጠይቀዋል።

https://p.dw.com/p/MiYf
ሜርክል ና ኤርዶጋንምስል AP
የቱርኩ ጠቅላይ ሚኒስትር ሬቼፕ ታይፕ ኤርዶጋን በበኩላቸዉ በቱርኩ ቋንቋ እራሱን የቻለ ትምህርት ቤት በጀርመን እንዲከፈት መጠየቃቸው ይታወሳል። መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል በሁለተኛ ቀን የቱርክ ጉብኝታቸዉ በጀርመን በቱርክ ቋንቋ ትምህርት ቤት ሊከፈት እንደሚችል በመግለጽ ይህ ግን የጀርመንኛ ቋንቋ እንዳያዉቁ ደንቃራ መሆን የለበትም ብለዋል ። የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ሃይለሚካኤል ከበርሊን ዘገባ ልኮልናል። ይልማ ሃይለሚካኤል፣ አዜብ ታደሰ ሂሩት መለሰ