1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአካል ጉዳተኞች የስፖርት ተሳትፎና ፈተናዎች

ዓርብ፣ የካቲት 28 2006

በሶቺ -ሩሲያ አካል ጉዳተኞች የሚሳተፉበት የክረምት ፓርኦሎምፒክስ ዛሬ ተጀምሯል። አካል ጉዳተኞች እንደማንኛውም ሰው በሁሉም ዓይነት የስፖርት ዘርፍ ተሳትፈው ውጤት ያስመዘግባሉ።

https://p.dw.com/p/1BLQD
Paralympics 2014 Sotschi Winterspiele
ምስል picture-alliance/dpa

ይሁንና ችሎታቸውን ማሳየት እንዲችሉ የነሱ ፍላጎት ብቻ ሳይሆን ለነሱ አስፈላጊ የሆኑ መገልገያዎች እና መሣሪያዎች መሟላት ይኖርባቸዋል። ሁለት የስፖርት ፍቅር ያላቸው ኢትዮጵያዊ አካል ጉዳተኞች መሳተፍ የሚፈልጉበትን የስፖርት ዘርፍ ገልፀውልናል።

Paralympics Sotchi 2014 - Skilanglauf
ምስል Getty Images

በምዕራቡ ዓለም አካል ጉዳተኞች አይሮፕላን ሲያበሩ፣ መኪና ሲነዱም ሆነ፣ ቅርጫት ኳስ ሲጫወቱ ማየት፤ አርዓያ ሆኖኛል ይላል ገብረ መድኅን ለምሳሌ። የክሊማንጃሮን ተራራ መውጣት ይፈልጋል። መሀሪም እንዲሁ የስፖርት አፍቃሪ ነው። ነገር ግን ብዙ ነገሮች አልተመቻቹለትም፤ ስለችግሮቹ ገልፆልናል።

ከዚህም ሌላ በአሁኑ ሰዓት አንድ የአካል ጉዳተኞች የልማት ማህበር ለመመስረት የሚያስፈልጉንን ሁሉ በሟሟላት ላይ እንገኛለን የሚለው ገብረ መድኅን ስለ አዲሱ ማህበር ዓላማ እና እንቅስቃሴ ነግሮናል።

ስለዚሁ አዲስ ማህበር እና ስለሁለቱ የስፖርት አፍቃሪ አካል ጉዳተኞች የበለጠ ለማወቅ የድምፅ ዘገባውን ይጫኑ።

ልደት አበበ

ሂሩት መለሰ