1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአወዛጋቢው ዳኛ ሹመት በአሜሪካ

ሰኞ፣ መስከረም 28 2011

በዩናይትድ ስቴትስ የሕግ መወሰኛ ምክር ቤት ይሁንታ በአብላጫ የድምፅ ድጋፍ የሀገሪቱ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኛ እንዲሆኑ ብሬት ካቫኖ ተወስኖላቸው ቃለ መሐላ ፈፅመዋል። ካቫኖ ለዚህ ታላቅ ኃላፊነት ከታጩበት ጊዜ አንስቶ ከፍተኛ ተቃውሞ እና ክርክር ያስከተሉ ሲሆን ሹመታቸው በቃለ መሐላ ፀድቆም ተቃዎሞው መቀጠሉ ይሰማል።

https://p.dw.com/p/36BT7
USA Senat bestätigt umstrittenen Richterkandidaten Kavanaugh | Innenraum mit Abstimmungsergebnis
ምስል Reuters/Senate TV

የፍትህ አካሉ ላይ የሚኖረው ተፅዕኖ

ሀገሪቱን የሚያስተዳድሩት የሪፐብሊካን እና ዴሞክራት የሕዝብ እንደራሴዎች ክፉኛ የተከፋፈሉባቸው ብሬት ካቫኖ ከትናንት በስተያ ከተሾሙበት የከፍተኛው ፍርድ ቤት ዳኝነታቸው አረፍተ ዘመን ካልገታቸው በቀር ለቀጣይ 3 አስርት ዓመታት ሊከርሙበት እንደሚችሉ ነው የተነገረው። በፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ጠቋሚነት የመጡት እና  የሪፐብሊካኖች ሙሉ ድጋፍ ያላቸው ዳኛ ሲመት ገለልተኛ ለሚባለው ለሀገሪቱ የፍትህ ሥርዓት ምን ማለት ይሆን?  ከዋሽንግተን የመገናኝ ብዙሃንን አስተያየት የቃኘው መክብብ ሸዋን ባጭሩ በስልክ አነጋግሬዋለሁ፤

መክብብ ሸዋ

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ