1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዉሮጳ ህብረትና ሩሲያ ጉባኤ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 28 2004

የአዉሮጳ ኅብረትና ሩሲያ 29ኛዉ ጉባኤ በሩሲያዋ ሴንትፒተርስበርግ ለሁለት ቀናት ተካሂዷል። ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት የጉባኤዉ ዋነኛ ትኩረት የሶርያ የወቅቱ ቀዉስ በመሆኑ ሁለቱ ወገኖች በሰፊዉ ተነጋግረዉበታል። በዚህም የደረሱበት የጋራ መግባቢያ

https://p.dw.com/p/158UG
ምስል Reuters

ሶርያን ከእርስበርስ ጦርነት ለመታደግ የአረቡ ሊግና የተመድ የሰየሟቸዉ ልዩ የሰላም ልዑክ ኮፊ አናን ያቀረቡት የሰላም እቅድ ተግባራዊ መሆን አማራጭ የለዉም የሚል እንደሆነ የኅብረቱ ፕሬዝደንት ኸርማን ቫንሮምፖይ ገልጸዋል። ይህም ተግባራዊ እንዲሆን ሁለቱም ወገኖች በጋራ የየበኩላቸዉን ጥረት ማድረግ እንደሚኖርባቸዉም ሮምፖይ አመልክተዋል። ከሁለቱ ወገኖች የሁለት ቀናት ስብሰባና ዉይይት በኋላ ለጋዜጠኞች የሩሲያዉ ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲንና ሮምፖይ ለ50 ደቂቃዎች ያህል ጋዜጣዊ መግለጫ ቢሰጡም፤ ፑቲን ሶርያን የሚመለከት አንዳችም ሃሳብ አለመተንፈሳቸዉ ነዉ የተነገረዉ።

ገበያዉ ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ