1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዉሮጳ ህብረት የአፍሪቃ ወታደራዊ ስምሪት

ሰኞ፣ ጥር 12 2006

የአዉሮጳ ህብረት መንግስት አልባ እየሆነች በመጣችዉ በማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ ወታደሮችን ለመላክ ዛሪ ብራስልስ ላይ ተስማማ። የህብረቱ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ካለፈዉ አጋማሽ ጀምሮ ቀዉስ በተጠናወታት በዚችዉ ሀገር ወታደሮቻቸዉን የሚልኩት እየተጠናከረ የመጣዉን ዉጥረት ለመግታት ነዉ።

https://p.dw.com/p/1Atxv
ምስል Getty Images/AFP/Miguel Medina

ጀርመን በበኩልዋ በማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ ተሰማርተዉ የሚገኙትን የአዉሮጳ ጦር ሃይላትን በአየር መጓጓዣ እና በአየር ላይ አዉሮፕላኖችን ነዳጅ በመሙላት ድጋፍ እንደሚሰጡ በሳምንቱ መጨረሻ የጀርመን ብዙሃን መገናኛዎች ዘግበዋል። 28 የአዉሮጳ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ብረስልስ ውስጥ በወታደሮቻቸው ስምሪት ላይ ስለመከሩበት ስብሰባ የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ ዘገባ ልኮልናል ።


ገበያዉ ንጉሴ
አዜብ ታደሰ
ኂሩት መለሰ