1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዉሮጳ ሕብረትና ስደተኞች

ረቡዕ፣ መስከረም 12 2008

ትናንት ብራስልስ-ቤልጅግ የተሠበሰቡት ሚንስትሮች በወሰኑት መሠረት የሕብረቱ አባል መንግሥታት ግሪክ፤ ኢጣሊያና ሐንጋሪ የሚገኙ አንድ መቶ ሥልሳ ሺሕ ስደተኞችን ይከፋፈላሉ።የሚንስትሮቹን ዉሳኔ ዛሬ የተሰየመዉ የመሪዎች ጉባኤ ያፀድቀዋል ተብሎ ይጠበቃል

https://p.dw.com/p/1GbsO
የአዉሮጳ ሕብረትና ስደተኞች
ምስል picture-alliance/AP Photo/Geert Vanden Wijngaert

የዜና መጽሔት መስከረም 11, 2008

የአዉሮጳ ሕብረት አባል መንግሥታት የሐገር አስተዳደር ሚንስትሮች ደቡባዊ አዉሮጳ የገቡ ስደተኞችን በኮታ ለመከፋፈል በአብላጫ ድምፅ ወሰኑ።ትናንት ብራስልስ-ቤልጅግ የተሠበሰቡት ሚንስትሮች በወሰኑት መሠረት የሕብረቱ አባል መንግሥታት ግሪክ፤ ኢጣሊያና ሐንጋሪ የሚገኙ አንድ መቶ ሥልሳ ሺሕ ስደተኞችን ይከፋፈላሉ።የሚንስትሮቹን ዉሳኔ ዛሬ የተሰየመዉ የመሪዎች ጉባኤ ያፀድቀዋል ተብሎ ይጠበቃል።የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጭምሮ የስደተኞች መብት ተቆርቋሪዎችን የአዉሮጳ ሕብረትን ዉሳኔ ለስደተኞቹ ችግር መፍትሔ የማይሆን በማለት እየተቹት ነዉ።የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ