1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዉሮጳ ሕብረትና ቡሩንዲ

ማክሰኞ፣ የካቲት 8 2008

ሚንስትሮቹ እንደሚሉት የቡሩንዲ ተቀናቃኝ ወገኖችን ለመሸምገል የሚደረገዉን ጥረት በተለይ የፕሬዝደንት ፔሪ ንኩሩንዚዛ መንግሥት እያደናቀፈ ነዉ።ማዕቀቡ መቼ እና በማን ላይ እንደሚጣል ግን ሚንስትሮቹ በግልፅ ያስታወቁት ነገር የለም።

https://p.dw.com/p/1HwJj
ምስል Getty Images/AFP/P. Moore

[No title]

የአዉሮጳ ሕብረት የቡሩንዲን ሠላም ያዉካሉ ባላቸዉ የሐገሪቱ ፖለቲከኞች ላይ የምጣኔ ሐብት ማዕቀብ እንደሚጥል አስጠነቀቀ።ትናንት ብራስልስ-ቤልጂግ ተሰብስበዉ የነበሩት የሕብረቱ አባል ሐገራት የዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮች እንዳስጠነቀቁት ቡሩንዲ ዉስጥ ሠላም ለማስፈን የሚደረገዉን ጥረት የሚያዉኩ ሐይላትን ሕብረታቸዉ በማዕቀብ ይቀጣል።ሚንስትሮቹ እንደሚሉት የቡሩንዲ ተቀናቃኝ ወገኖችን ለመሸምገል የሚደረገዉን ጥረት በተለይ የፕሬዝደንት ፔሪ ንኩሩንዚዛ መንግሥት እያደናቀፈ ነዉ።ማዕቀቡ መቼ እና በማን ላይ እንደሚጣል ግን ሚንስትሮቹ በግልፅ ያስታወቁት ነገር የለም። የብራስልሱ ወኪላችን ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሠ