1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዉሮጳ ሕብረትና ቱርክ

ዓርብ፣ መጋቢት 9 2008

የሕብረቱ አባል ሐገራት መሪዎች እና የቱርክ ጠቅላይ ሚንስትር ከዚሕ ቀደም ያደረጉትን ስምምነት ዛሬ አፀደቁ። ይሁንና ሁለቱ ወገኞች ቱርክ እንዲሟላላት ካቀረበቻቸዉ ነጥቦች በአንዳዶቹ ላይ ባለመግባባታቸዉ እስካሁን ድረስ ስምምነቱን አልተፈራረሙም ነበር።

https://p.dw.com/p/1IFyu
ምስል Reuters/S. de Sakutin

[No title]

የአዉሮጳ ሕብረት እና የቱርክ ባለሥልጣናት «ሕገ-ወጥ» የሚሏቸዉ ሥደተኞች ወደ አዉሮጳ እንዳይገቡ ለማገድ ከዚሕ ቀደም በተስማሙበት ነጥብ ላይ የሚያደርጉት ድርድር በስምምነት አጠቃለዋል። የሕብረቱ አባል ሐገራት መሪዎች እና የቱርክ ጠቅላይ ሚንስትር ከዚሕ ቀደም ያደረጉትን ስምምነት ዛሬ አጽድቀዋል። ሁለቱ ወገኞች ቱርክ እንዲሟላላት ካቀረበቻቸዉ ነጥቦች በአንዳዶቹ ላይ ባለመግባባታቸዉ ረዘም ላሉ ሰዓታት ስምምነቱን ሳይፈራረሙ ሲደራደሩ ነበር የዋሉት። በሌላ በኩል የሁለቱ ወገኖች መሪዎች ተስማሙም ተፋረሱ ዓላማቸዉን የመብት ተሟጋቾች እየተቃወሙት ነዉ።ሥምምነቱ ከመፅደቁ ጥቂት ቀደም ብሎ የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ የሚከተለዉን ዘገባ ልኮልናል።

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ