1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዉሮጳ ሕብረት እና የብሪታንያ ድርድር

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 23 2009

ባለሥልጣናቱ ከዚሕ ቀደም ባደረጉት ሁለት ዙር ድርድር የዜጎች መብት፤የአየር ላንድ ወሰን እና ብሪታንያ ለሕብረቱ መክፈል በሚገባት የገንዘብ መጠን ላይ ቅድሚያ ሰጥተዉ ለመደራደር ተስማምተዉ ነበር

https://p.dw.com/p/2j2bD
Brüssel Brexit-Verhandlungen, David Davis & Michel Barnier
ምስል Reuters/Y. Herman

የአዉሮጳ ሕብረት እና የብሪታንያ ድርድር

የብሪታንያ እና የአዉሮጳ ሕብረት ባለሥልጣናት ብሪታንያ ከሕብረቱ አባልነት ሥለምትወጣበት ሥልት የጀመሩትን ድርድር ትናንት ለሰወስተኛ ጊዜ ቀጥለዋል።ባለሥልጣናቱ ከዚሕ ቀደም ባደረጉት ሁለት ዙር ድርድር የዜጎች መብት፤የአየር ላንድ ወሰን እና ብሪታንያ ለሕብረቱ መክፈል በሚገባት የገንዘብ መጠን ላይ ቅድሚያ ሰጥተዉ ለመደራደር ተስማምተዉ ነበር።ትናንት በተጀመረዉ ድርድር ግን ተደራዳሪዎቹ በሰወስቱ ጉዳዮች ላይ የተግባቡ አይመስሉም።ድርድሩ እስከ ሐሙስ ይቀጥላል ተብሏል።የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ