1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዉሮጳ ሕብረት ዉሳኔና ኢትዮጵያ

ዓርብ፣ መስከረም 28 2014

ሽትራስቡርግ-ፈረንሳይ ትናንት የተሰየመዉ ምክር ቤት ባሳለፈዉ ባለ 29ኝ ነጥብ ዉሳኔ፣ ተፋላሚ ኃይላት ሠላማዊ ሰዎችንና ተቋማትን እንዳያጠቁ፣ ለችግረኛዉ ሕዝብ ርዳታ ይደርስ ዘንድ እንዲፈቅዱ፣ የአማራ ክልል ታጣቂዎች ከትግራይ፣ የትግራይ ታጣቂዎች ደግሞ ከአማራና አፋር ክልሎች እንዲወጡ ጠይቋልም

https://p.dw.com/p/41SBJ
Straßburg | Plenarsitzung Europäisches Parlament
ምስል Frederick Florin/AFP/AP/dpa/picture alliance

ተፋላሚዎች ተኩስ አቁመዉ እንዲደራደሩ ፓርላማዉ ጠይቋል

 የኢትዮጵያ መንግስትና የሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ (ሕወሓት) የገጠሙትን ጦርነት ባስቸኳይ አቁመዉ እንዲደራደሩ የአዉሮጳ ሕብረት ምክር ቤት (ፓርላማ) በድጋሚ አሳሰበ።ሽትራስቡርግ-ፈረንሳይ ትናንት የተሰየመዉ ምክር ቤት ባሳለፈዉ ባለ 29ኝ ነጥብ ዉሳኔ፣ ተፋላሚ ኃይላት ሠላማዊ ሰዎችንና ተቋማትን እንዳያጠቁ፣ ለችግረኛዉ ሕዝብ ርዳታ ይደርስ ዘንድ እንዲፈቅዱ፣ የአማራ ክልል ታጣቂዎች ከትግራይ፣ የትግራይ ታጣቂዎች ደግሞ ከአማራና አፋር ክልሎች እንዲወጡ ጠይቋልም።የሕብረቱ አባል ሐገራት ለተፋላሚዎች የጦር መሳሪያ እንዳይሸጡ አግዷልም።ተፋላሚ ኃይላት ጦርነቱን ለማስቆም እስከያዝነዉ የጎርጎሪያኑ ጥቅምት መጨረሻ ድረስ ሁነኛ ርምጃ ካልወሰዱ ሕብረቱ ማዕቀብ እንደሚጥልም ምክር ቤቱ አስጠንቅቋል።

ገበያዉ ንጉሴ 

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ