1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዉሮጳ ሚኒስትሮች ጉባኤ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 16 2008

በሶሪያ እና ኢራቅ ያሉ ሁኔታዎችን ለማሻሻል የአዉሮጳ ኅብረት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ትናንት ብራስልስ ላይ ተሰብስበዉ መክረዋል።

https://p.dw.com/p/1ItiU
Belgien EU Kommission Flaggen Großbritannien und Europa
ምስል Reuters/Y. Herman

[No title]

ሚኒስትሮቹ በዚህ ጉባኤያቸዉ በአካባቢዉ ራሱን የሶርያ እና ኢራቅ እስላማዊ መንግሥት ብሎ በመሰየም የሚንቀሳቀሰዉን ፅንፈኛ ቡድን ISISን ስጋት ለመቀነስም የሚከተሉትን ስልት አጠናክረዉ እንደሚቀጥሉም ገልጸዋል። ከዚህም ሌላ የአዉሮጳ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጉባኤ በደቡብ ሱዳን እና በዴሞክራቲክ ሪፑብሊክ ኮንጎ ጉዳይ ላይም መወያየቱን እና የኅብረቱን አቋም ግልጽ ያደረገ መግለጫም ማዉጣታቸዉን የብራስልሱ ዘጋቢያችን ገበያዉ ንጉሤ የላከልን ዘገባ ያስረዳል።

ገበያዉ ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ