1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዉሮጳ ኅብረትና የሕንድ ትብብር

ሐሙስ፣ መጋቢት 22 2008

ሕንድና የአዉሮጳ ኅብረት ተባብረዉ ለመስራት የተስማሙት እንደ ጎርጎርያኑ አቆጣጠር በ2004 ነዉ። የቤልጂጓ ርዕሠ-ከተማ ብራሥልስ በአሸባሪዎች ከተጠቃች ወዲሕ የመሪዎች ጉባኤ ስታስተናግድ የትናንቱ የመጀመሪያዋ ነዉ።

https://p.dw.com/p/1INPY
ምስል Reuters/Y. Herman

[No title]

የአዉሮጳ ኅብረትና ሕንድ የንግድ፤ የመዋዕለ ነዋይ ፍሰት እና የፀረ-ሽብር ትግል ትብብራቸዉን አጠናከረዉ እንደሚቀጥሉ የሁለቱ ወገኞች መሪዎቹ አረጋገጡ። ትናንት ብራስልስ ቤልጂግ ዉስጥ የተወያዩት የአዉሮጳ ሕብረት እና የሕንድ መሪዎች በጉባኤያቸዉ ማብቂያ እንዳሉት 12 ዓመት ያስቆጠረዉን የትብብር ሥምምነታቸዉን ይበልጥ ያጠናክራሉ። ሕንድና የአዉሮጳ ኅብረት ተባብረዉ ለመስራት የተስማሙት እንደ ጎርጎርያኑ አቆጣጠር በ2004 ነዉ።የቤልጂጓ ርዕሠ-ከተማ ብራሥልስ በአሸባሪዎች ከተጠቃች ወዲሕ የመሪዎች ጉባኤ ስታስተናግድ የትናንቱ የመጀመሪያዋ ነዉ። የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ ዝርዝር ዘገባ አለዉ።

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ