የአዉሮጳ ኅብረትና የሩስያ ዉዝግብ
ማክሰኞ፣ መስከረም 5 2013ማስታወቂያ
የሩስያና አዉሮጳ ግንኙነት በተለይ በቤላ ሩስ ከተቀሰተዉ የፖለቲካ ቀዉስ እና ከታዋቂዉ ፖለቲከኛ አሌክሴይ ናቫልኒ መመረዝ በኋላ ከፍተና ችግር ዉስጥ ገብቶአል። አዉሮጳ ሞስኮን ቤላሩስያዉያን ምርጫ አጭበርብረዋል የሰብዓዊ መብት ጥሰዋል የሚልዋቸዉን ፕሬዚዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ በመደገፍ እና የፕሬዚዳንት ፑቲንን መንግሥት በመተቸት የሚታወቀዉን አሌክሴይ ናቫልኒን በመመረዝ ይከሳል። ሩስያ ግን የቀረበባትን ክስ አትቀበልም። እንደዉም በቤላሩስ ለተከሰተዉ ቀዉስ አዉሮጳዉያን እና ሌሎች ጣልቃ ገብነት አስተዋፅኦ እያደረገ ነዉ ስትል ታማርራለች። የናቫልኒ መመረዝ ጉዳይም መረጃ የማይቀርበት ሞስኮን የማጠልሸት ተግባር ነዉ ስትል ትከራከራለች። እያደገ እና እየሰፋ የሄደዉ የቤላሩስያዉያን ፀረ ሉካሼንኮ ተቃዉሞ እና የናቫልኒ የሕክምና ዉጤት ይህን የሁለቱን ወገኖች ዉዝግብ እና አለመግባባት እየሠፋዉ እና እያከረረዉ የሚሄድ እንጂ የሚያላላዉ ብሎም የሚያለዝበዉ አልሆነም።
ሙሉ መሰናዶዉን የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን ይከታተሉ !
ገበያዉ ንጉሴ
አዜብ ታደሰ