1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዉሮጳ ኅብረትና የቱርክ የስደተኞች ሰፈራ

ማክሰኞ፣ መጋቢት 27 2008

ስደተኞቹን ከአንድ ሃገር ወደ ሌላዉ ሃገር የመመለሱ ተግባር በርካታ ተቃዉሞ ና ትችት እየቀረበት ነዉ። ቅሪታቸዉን ከሚያሰሙት መካከል ለሰብዓዊ መብት መከበር የሚከራከሩ ድርጅቶች ግንባር ቀደሞች ናቸዉ።

https://p.dw.com/p/1IPl3
የአዉሮጳ ኅብረትና የቱርክ የስደተኞች ሰፈራ
ምስል Reuters/G. Moutafis

[No title]

የአዉሮጳ ኅብረት ስደተኞች ወደ ግዛቱ እንዳይገቡ ለማገድ ከቱርክ ጋር በገባዉ ዉል መሠረት ስደተኞችን ከግሪክ ወደ ቱርክ እንዲሁም ከቱርክ ወደ ሌሎች የአውሮጳ ሃገራት የማሻገሩ ሥራ ጀምሮአል። በትናንትናዉ ዕለት 32 የሶሪያ ስደተኞች ከኢስታንቡል ቱርክ ወደ ሰሜንዊቷ የጀርመን ከተማ ሃኖቨር ገብተዋል። ፊንላንድም 11 የሶሪያ ስደተኞችን አስገብታለች። ስደተኞቹን ከአንድ ሃገር ወደ ሌላዉ ሃገር የመመለሱ ተግባር በርካታ ተቃዉሞ ትችት እየቀረበት ነዉ። ቅሪታቸዉን ከሚያሰሙት መካከል ለሰብዓዊ መብት መከበር የሚከራከሩ ድርጅቶች ግንባር ቀደሞች ናቸዉ። የቱርክና የግሪክ ነዋሪዎችም የስደተኞቹን ከቦታ ቦታ የማዘዋወር እርምጃ በሰልፍ እየተቃወሙትዉ። የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለሚካኤል፤ ቶማስ ቦርማን የዘገበዉን እንዲህ አቀናብሮታል።

ይልማ ኃይለሚካኤል

አዜብ ታደሰ