1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዉሮጳ ኅብረት ለአባላቱ ድጋፍ እሰጣለሁ አለ

ረቡዕ፣ መጋቢት 9 2012

ከሚወስዷቸው የጥንቃቄ እርምጃዎች ጎን ለጎን ህብረቱ የከፋ የኢኮኖሚ  ጉዳት ለሚያጋጥማቸው አባል ሃገራቱ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል።

https://p.dw.com/p/3ZfGb
Brüssel EU-Flaggen vor Kommissions-Gebäude
ምስል Reuters/F. Lenoir

ህብረቱ ለአባል ሃገራቱ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል

የኮረና ተዋሕሲ ክፉኛ እየተሰራጨበት ባለበት አውሮጳ፤ የሕብረቱ አባል ሃገራት የተዋህሲውን ስርጭት ለመግታት ከሚወስዷቸው የጥንቃቄ እርምጃዎች ጎን ለጎን ህብረቱ የከፋ የኢኮኖሚ ጉዳት ለሚያጋጥማቸው አባል ሃገራቱ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል። ተዋህሲው ክፉና የተሰራጨባቸው አብዛኞቹ አባል ሃገራት ድንበሮቻቸውን ከመዝጋት ባሻገር ዜጎቻቸው ከቤት እንዳይወጡ የሚያስገድዱ ክልከላዎችን መጣል ጀምረዋል።


ገበያው ንጉሴ
ታምራት ዲንሳ