1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዉሮጳ ኤኮኖሚ በ2015

ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 20 2008

ነገ የሚሠናበተዉ የጎርጎሪያኑ 2015 ለአዉሮጳ ምጣኔ ሐብት የጥሩም የመጥፎም ክስተት ዓመት ነዉ። ፖርቱጋል፤ አየርላንድ እና ስጳኝ በቀዳሚዎቹ ዓመታት ካጋጠማቸዉ ኪሳራ ያንሰራሩ ሲሆን ግሪክን ያሸመደመደዉ ምጣኔ ሐብታዊ ድቀት ግን ሁነኛ መፍትሔ ያገኘ አይመስልም

https://p.dw.com/p/1HWCo
ምስል picture-alliance/dpa

የአውሮፓ ኤኮኖሚ በ2015

ነገ የሚሠናበተዉ የጎርጎሪያኑ 2015 ለአዉሮጳ ምጣኔ ሐብት የጥሩም የመጥፎም ክስተት ዓመት ነዉ። ፖርቱጋል፤ አየርላንድ እና ስጳኝ በቀዳሚዎቹ ዓመታት ካጋጠማቸዉ ኪሳራ ያንሰራሩ ሲሆን ግሪክን ያሸመደመደዉ ምጣኔ ሐብታዊ ድቀት ግን ሁነኛ መፍትሔ ያገኘ አይመስልም።አጠቀላዩ የአዉሮጳ ምጣኔ ሐብትም መጠነኛ ዕድገት ቢያስመዘግብም ዕድገቱ የሚያወላዳ አይነት አይደለም።የዛሬዉ ከኢኮኖሚዉ ዓለም ዝግጅታችን የአዉሮጳን ምጣኔ ሐብት ይዞታን ይቃኛል።የብራስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ አጠናቅሮታል።

ገበያዉ ንጉሴ

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ