1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮጳ ህብረት፣ ሩስያ እና ዩክሬይን

ሐሙስ፣ የካቲት 27 2006

የአውሮጳ ህብረት አባል ሀገራት ርዕሳነ ብሔር እና መራሕያነ መንግሥት ስርጭታችን ይተላለፍ በነበረበት ጊዜ በብራስልስ ተገናኝተው ስለ ዩክሬይን ውዝግብ እየመከሩ ነበር። በዚሁ መሪዎቹ በጠሩት ልዩ ጉባዔ ላይ ሩስያ ህገ ወጥ የምትለው፣ አውሮጳውያኑ ግን ዕውቅና የሰጡት የዩክሬይን የሽግግር መንግሥት ጠቅላይ ሚንስትር አርሰኒ ያዜንዩክ ተገኝተዋል።

https://p.dw.com/p/1BLQv
ምስል Reuters

አውሮጳውያኑ መሪዎች ዓለም አቀፍ ህግን በመጣስ የዩክሬይንን የክሪሚያ ግዛት ይዛለች ባሏት ሩስያ ላይ አሳማኝ እና አንድ የሆነ ርምጃ ለመውሰድ የሚችሉበትን መንገድ ለማፈላለግ ነው የተሰበሰቡት። ግን በመሪዎቹ መካከል የሀሳብ ልዩነት መኖሩ እንደታየ ነው የሰማነው። አንዳንዶች ጀርመን እና ኢጣልያን የመሳሰሉ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊውን መንገድ ማስቀደም ሲፈልጉ፣ ሌሎች በተለይ ከሩስያ ጋ የተጎራበቱት ሀገራት በሩስያ አንፃር ጠንካራ ርምጃ እንዲወሰድ ይመርጣሉ። ጉባዔውን እየተከታተለ ያለውን የብራስልስ ወኪላችን ገበያው ንጉሤን ከልዩ ጉባዔው ምን ዓይነት ውጤት እንደሚጠበቅ ከስቱድዮ በቀጥታ በስልክ ጠይቄው ነበር፣ ቀጣዩን ማብራሪያ ሰጥቶኛል።

ገበያው ንጉሤ

አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ