1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮጳ ህብረት ኮሚሽን ርዳታ ለድርቅ ተጎጂዎች

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 4 2008

የአውሮጳ ህብረት ኮሚሽን ባለፈው ዓርብ እንዳስታወቀው፣ በኢትዮጵያ በተከሰተው ድርቅ የተጎዱትን ለመርጃ ተጨማሪ 122,5 ሚልዮን ዩሮ ርዳታ ይሰጣል።

https://p.dw.com/p/1IU5B
Brüssel Gebäude der Europäischen Kommission
የአውሮጳ ህብረት ኮሚሽንምስል Reuters/Y. Herman

[No title]

የአውሮጳ ህብረት የውጭ ጉዳይ ተጠሪ ፌዴሪካ ሞገሪኒን ጨምሮ የአውሮጳ ህብረት ኮሚሽነሮች በአዲስ አበባ ከአፍሪቃ ህብረት ኮሚሽን አቻዎቻቸው ጋር የሁለትዮሽ መደበኛ ስብሰባቸውን ባካሄዱት ወቅት ነበር ኮሚሽኑ ርዳታው እንደሚሰጥ ይፋ ያደረገው። ሞጌሪኒ ከኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ቴድሮስ አድሀኖም ጋር ሲወያዩ፣ ሌሎቹ ኮሚሽነሮች ወደ ሶማሌ ክልል ተጉዘዋል። የብረስልሱ ወኪላችን የኮሚሽኑን ቃል አቀባይ አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሮዋል።

ገበያው ንጉሤ

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ