1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮጳ ሕብረትና የአፍሪቃ ሃገራት ጉባዔ በማልታ

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 30 2008

የአውሮጳ ሕብረት የሀገር መሪዎች እና ከ30 በላይ የአፍሪቃ ሀገራት መሪ እና ተወካዮች የሚሳተፉበት ጉባኤ ነገ፤ ረቡዕ በትንሿ የማልታ ደሴት መዲና ቫሌታ ይካሄዳል። የጉባኤው ዓቢይ ትኩረት በአውሮጳ ለሚታየው የስደተኞች ቀውስ እና ለተገን ጠያቂዎች ጉዳይ መፍትሔ ማፈላለግ ነው።

https://p.dw.com/p/1H3cj
Symbolbild Flüchtlingsboot Küste Libyen
ምስል Reuters/D. Zammit Lupi

[No title]

የአውሮጳ ሕብረት ስደተኞች ከሚመጡባቸው ወይም ከሚሸጋገሩባቸው የአፍሪቃ ሀገራት ጋር አብሮ ለመስራት የማልታው ጉባኤ እድል ይፈጥራል ብሎ ያምናል። ይሁንና ፣ ሌሎች ይህን ያህል ባለ ሙሉ ተስፋ አይደሉም። የአፍሪቃ መሪዎች የሚያሳስቧቸው ሌሎች ቀውሶች አሉ። በዚያ ላይ ከአውሮጳ የተገባላቸው ድጋፍ ቃል መሠረት ባለፉት ጊዜያት እንደጠበቁት ሳይቀርብላቸው መቅረቱ ተስተውሏል። ለምሳሌ የአውሮጳ ኮሚሽን፣ የአውሮጳ መንግሥታት ለአፍሪቃ ስደተኞች እንደሚሰጡት ካስታወቀው 1,8 ቢሊዮን ዮሮ እስካሁን የቀረበው 47 ሚሊዮን ዮሮ ብቻ ነው። ይህ የአፍሪቃ ሃገራቱ በነገው ጉባኤ ላይ የሚደራደሩበት አንዱ ርዕስ ይሆናል። በዚሁ ሁለት ቀናት በሚቆየው ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሀምሳ የሚበልጡ የአውሮጳ ሕብረትና የአፍሪቃ ሃገራት መሪዎች ተካፋይ ይሆናሉ። ስለማልታው ጉባዔ ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ተወልደ ሙሉጌታን አነጋግሮ ቀጣዮን ዘገባ ልኮልናል።


ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ


ልደት አበበ
አርያም ተክሌ