1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮጳ ሕብረት አባል ሃገራት ተቃውሞ

ዓርብ፣ የካቲት 29 2011

ኮሚሽኑ ባንኮቻቸውን እና የፋይናንስ ስርዓቶቻቸው ለሀሰተኛ የገንዘብ ዝውውርና ሀሰተኛ የፋይናንስ ድጋፍ ለመስጠት የተጋለጡ ናቸው ሲል ያቀረበውን የ23 ሀገራት ዝርዝር የህብረቱ አባል ሀገራት ሳይቀበሉት ቀርተዋል። አባላቱ ዝርዝሩን የተቃወሙት ኮሚሽኑ ከ3 ሳምንት በፊት በዝርዝሩ ውስጥ ትካተት ያለው ሳዑዲ አረብያ ከፍተኛ ግፊት ካደረገች በኋላ ነው።

https://p.dw.com/p/3Egmf
Belgien Europäische Kommission in Brüssel
ምስል picture-alliance/dpa/D. Kalker

የአውሮጳ ህብረት አባል ሀገራት ተቃውሞ

የአውሮጳ ህብረት አባል ሀገራት የሀገር ውስጥ እና የፍትህ ሚኒስትሮች ትናንት ባካሄዱት ስብሰባ ከዚህ ቀደም የህብረቱ ኮሚሽን ያቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ተቃውሟል። ኮሚሽኑ ባንኮቻቸውን እና የፋይናንስ ስርዓቶቻቸው ለሀሰተኛ የገንዘብ ዝውውርና ለሀሰተኛ የፋይናንስ ድጋፍ ለመስጠት የተጋለጡ ናቸው ሲል ያቀረበውን የ23 ሀገራት ዝርዝር የህብረቱ አባል ሀገራት ሳይቀበሉት ቀርተዋል። አባላቱ ዝርዝሩን የተቃወሙት ኮሚሽኑ ከሥስት ሳምንት በፊት በዝርዝሩ ውስጥ ትካተት ያለው ሳዑዲ አረብያ ከፍተኛ ግፊት ካደረገች በኋላ መሆኑ ይነገራል። የህብረቱ አባል ሀገራት ባወጡት መግለጫ ግን እቅዱን የተቃወሙት ኮሚሽኑ ያቀረበው መዘርዝር ግልጽ በሆነ ሂደት ባለመዘጋጀቱ እና ሀገራትም እርምጃ እንዲወስዱ የማያበረታታ ባለመሆኑ ነው ብለዋል።
ገበያው ንጉሴ
ኂሩት መለሰ
ተስፋለም ወልደየስ