1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የሲቪክ ማሕበራት እና ምርጫ

ሰኞ፣ ግንቦት 12 2011

በዘርፉ የተሰማሩ የሲቪክ ማሕበራት በጉዳዩ ላይ በኢትዮጵያ የአውሮጳ ሕብረት ጽሕፈት ቤት ተጠሪዎች በተገኙበት ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ውይይት አካሂደዋል። የውይይቱ ተሳታፊዎች የአውሮጳ ሕብረት የሲቪል ማኅበረሰብ ፈንድ ለዘርፉ ከሚሰጠው ድጋፍ በተጨማሪ ሌሎች መንግሥታት የሚሰጡት እገዛም በመጪው ምርጫ የኅብረተሰቡን ተሳትፎ ከፍ ለማድረግ ይረዳል።

https://p.dw.com/p/3InXI
Äthiopien EU Wahlunterstützung
ምስል DW/G. Tedla

በምርጫው የህብረተሰቡን ተሳትፎ ለማሳደግ የሲቪክ ማህበራት ድጋፍ ያሻቸዋል።

በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ኅብረተሰቡን ግንዛቤ ለማስጨበጥ የሚሰሩ የሲቪክ ማሕበራት የሚያገኙት ድጋፍ ጠቃሚ መሆኑ ተገለፀ። በዘርፉ የተሰማሩ የሲቪክ ማሕበራት በጉዳዩ ላይ በኢትዮጵያ የአውሮጳ ሕብረት ጽሕፈት ቤት ተጠሪዎች በተገኙበት ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ውይይት አካሂደዋል። ዶይቼ ቬለ ያነጋገራቸው የውይይቱ ተሳታፊዎች እንዳሉት የአውሮጳ ሕብረት የሲቪል ማኅበረሰብ ፈንድ ለዘርፉ ከሚሰጠው ድጋፍ በተጨማሪ ሌሎች መንግሥታት የሚሰጡት እገዛም በመጪው ምርጫ የኅብረተሰቡን ተሳትፎ ከፍ ለማድረግ ይረዳል። የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ተጨማሪ ዘገባ አለው።


ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
ተስፋለም ወልደየስ