1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮጳ ኅብረትና የብሪታንያ ፍቺ

ማክሰኞ፣ ጥር 4 2013

የብሪታንያ ህዝብ በጠባብ ልዩነት ኅብረቱን ለቆ መውጣትን (ብሬግዚትን)  በመረጠ በ4 ዓመት ተኩል ነው ብሪታንያ ከኅብረቱ የተለየችው። ከአስቸጋሪ  ድርድሮች በኋላ ኅብረቱና ብሪታንያ በስምምነት ተለያይተዋል።ከጎርጎሮሳዊው ጥር 1 2021 ዓም አንስቶ የሁለቱ ወገኖች ግንኙነት በአዲሱ የንግድና የትብብር ስምምነት መሠረት እየተካሄደ ነው።

https://p.dw.com/p/3npRu
Standbild Dokumentation | KW1 | Brexit Bittersüß
ምስል DW

የአውሮጳ ኅብረትና የብሪታንያ ፍቺ

 

ብሪታንያ ከአውሮጳ ኅብረት አባልነት በይፋ ከወጣች 12 ቀናት ተቆጥረዋል።በጎርጎሮሳዊው 2016 በአውሮጳ ኅብረት አባልነት መቀጠል አለያም ኅብረቱን ለቆ መውጣት የሚሉ ሁለት ምርጫዎች የተሰጡት የብሪታንያ ህዝብ በጠባብ ልዩነት ኅብረቱን ለቆ መውጣትን (ብሬግዚትን)  በመረጠ በ4 ዓመት ተኩል ነው ብሪታንያ ከኅብረቱ የተለየችው። በነዚህ ጊዜያት ከተካሄዱ አስቸጋሪ  ድርድሮች በኋላ ኅብረቱና ብሪታንያ በስምምነት ተለያይተዋል።ከጎርጎሮሳዊው ጥር 1 2021 ዓም አንስቶ የሁለቱ ወገኖች ግንኙነት ከሁለት ሳምንት በፊት በተስማሙበት በአዲሱ የንግድና የትብብር ስምምነት መሠረት እየተካሄደ ነው።ስለ ድርድሩ ሂደት እና  ሁለቱ ወገኖች ከሁለት ሳምንት በፊት ስለደረሱበት የንግድና የትብብር ስምምነት የመጀመሪያዎቹ ቀናት አተገባበር የብራሰልሱ ዘጋቢያችን ገበያው ንጉሴ የለንደኑ ዘጋቢያችን ድልነሳ ጌታነህና የፓሪስዋ ዘጋቢያችን ሃይማኖት ጥሩነህ ባለፈው ሳምንት አስተያየቶቻቸውን አካፍለውናል። ዛሬ የሚቀርበው የመጨረሻው ክፍል፣ በንግድና ትብብር ስምምነቱ ምንነት እንዲሁም ወደፊት ሊያጋጥሙ ይችላሉ ተብለው በሚያሰጉ ጉዳዮች ላይ ያተኩራል። 

ኂሩት መለሰ

ገበያው ንጉሴ

ድልነሳ ጌታነህ

ሃይማኖት ጥሩነህ