1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮፓው ኅብረትና ጦር መሣሪያ፧

ረቡዕ፣ ኅዳር 8 1997

ከአውሮፓው ኅብረት አባል መንግሥታት መካከል፧ ብሪታንያ፧ ፈረንሳይ፧ ጀርመን፧ ኢጣልያና ስዊድን፧ በዓለም-አቀፍ ደረጃ የታወቁ፧ ጦር መሣሪያ ሻጮች መሆናቸው የታወቀ ነው። የጦር መሣሪያ ሽያጭን በተመለከተ፧ ኀላፊነቱ የየብሔራዊ መንግሥታቱ ሲሆን፧ የአውሮፓ ፓርላማ የህዝብ እንደራሴዎች፧ ሐሳብ ከማቅረብና ከማስጠንቀቅ በስተቀር የሚወስዱት እርምጃ የለም። የጦር መሣሪያ ሽያጭን በተመለከተ፧ ትናንት የተጀመረው ክርክር፧ ዛሬም ቀጥሏል።

https://p.dw.com/p/E0fD

ከአውሮፓው ኅብረት የጦር መሣሪያ ሽያጭን በተመለከተ፧ የአውሮፓ ፓርላማ የህዝብ, እንደራሴዎች፧ እጅ የታሠረ ነው። አንዳብድ አሳሳቢ ሁኔታዎች በሚያጋጥሙበት ጊዜ፧ መከራከር ብቻ ሳይሆን ክስ ብጤ የሚያቀርቡበት ሁኔታም አለ። የፓርላማው አባላት ያቀረቡትን ክስ ፧ ከእስፓኝ የተወከሉት የህዝብ እንደራሴ Raul Romeva Rueda፧ አጠቃለው በዘገባ መልክ አቅርበውታል። ፳፮ ገጾች ባሉት ሰነድ፧ ሮሜቫ Rueda፧ የአንዳንዶቹ መንግሥታት የጦር መሣሪያ ሽያጭ አጠያያቂ መሆኑን ከማመላከታቸውም፧ እ ጎ አ ከ ፲፱፻፺፰ ዓ ም የወጣው የጦር መሣሪያ ሽያጭ ነክ ደንብ እንዲከበር ማድረጊያው ሰዓት አሁን ነው ይላሉ።
O-tone(The maine problem......
«ዋናው ችግር፧ እንደሚታወቀው መንግሥታቱ፧ መመሪያውን ደንብ ተግባራዊ አለማድረጋቸው ነው። እርግጥ ነው፧ መመሪያ ደንቡም ቢሆን ራሱ ችግር ነበረበት። በአሣሪ ድንጋጌነቱም ሆነ መሣሪያነቱ፧ በጣም ደካማ ነበረ ማለት ይቻላል። ደንቡን ችላ ብሎ ለመሥራት የሚያግድ ሁኔታ አልነበረም። የጦር መሣሪያ ሽያጭን ወይም አቅርቦትን መቆጣጠር የሚያስችል ግልጽ አሠራር የተጓደለ ነው።
መመሪያው ደንብ በግልጽ እንደሚየስረዳው፧ ጦር መሣሪያ ለሰብአዊ መብት መርገጫ ሊውል ለሚችልበት አካባቢ መሸጥ የለበትም። የአካባቢዎች ግጭት ወደሚከሠትበት፧ ህዝብን ለከፋ ድህነት የሚዳርግ ጠንቅ ወደአለበት አካባቢ ጦር መሣሪያ እንዳይላክ ሰነዱ ወይም ደንቡ ያሳስባል ይጠይቃል እንጂ አሣሪነት የነበትም። ፹ ከመቶው የጦር መሣሪያ የሚሸጠው ከአውሮፓ ውጭ ለሚገኙ አገሮች ነው። ሮሜቫ ሩኤዳ፧ በተለይ፧ ሰብአዊ መብት ለሚረግጡ አገሮች፧ ጦር መሣሪያ መሸጡን አጥብቀው ነው የነቀፉት። ከተሸጡት የጦር መሣሪያዎች መካከል፧ ቁም-ሥቅል ማሳያ መሣሪያዎች፧ እንዲሁም ሙት በቃ ለተበየነበት ሰው ነፍሱ እንድታልፍ ማድረጊያ መሣሪያ፧ ፧ ሠራ አካላትን በሥቃይ የሚያነዝር የኤሌክትሪክ መሣሪያና የመሳሰሉት መሸጣቸው ሮሜቫ ሩኤዳን እጅግ ነው ያሳዘናቸው። አንዳንዶቹን ቁም ሥቅል ማሣያ መሣሪያዎች፧ ፖሊሶች በጥርጣሬ የተያዙ ሰዎችን ለማናዘዝ ያውሏቸዋል። የአውሮፓ ፓርላማ አባላት፧ በተለይ በቻይና ላይ የተጣለው የጦር መሣሪያ እገዳ እንዲነሣ አይፈልጉም። እ ጎ አ በ ፻፺፻፹፱ ዓ ም የተደነገገው የጦር መሣሪያ ሽያጭ እገዳ እንዳይነሣ ቢባልም፧ ጀርመንና ፈረንሳይ ያላቸውን ዝንባሌ መንስዔ በማድረግ፧ የአውሮፓው ምክር ቤት በመመርመር ላይ ሲሆን፧ ወግ አጥባቂው የህዝብ እንደራሴ፧ ቶማስ ማን እንደሚሉት እገዳ ማንሳት፧ ጨርሶ ሊታሰብ የማይገባው ጉዳይ ነው። በአውሮፓ ፓርላማ፧ የቲቤት ጉዳይ ተመልካች ቡድን ፕሬዚዳንት ቶማስ ማን በቻይና፧ በቅድሚያ የሰብአዊ መብት ይዞታ ተሻሽሎ መገኘት እንደሚኖርበት ነው የሚያሳስቡት።
O-ton(
«ይሁንና ቅድመ-ግዴታዎቹ ተሟልተው አይገኙም። የአውሮፓው ኅብረት በየትኛውም ቦታ፧ ሰብአዊ መብት መከበሩን እንድንከታተል ነው መመሪያው የሚያስገነዝበን። የፖለቲካ አመለካከታችን መሠረተ-ሐሳብም በዚህ ላይ የተመረኮዘ ነው። ወደሌላ አቅጣጫ ማምራት የለበትም። ለገበያ በሚቀርብ ምርት ወይም ሸቀጣ-ሸቀጥ ላይ እጅግ በማትኮር፧ የሚያስቀጡ ሁኔታዎች ችላ ይባላሉ« ሲሉ ገልጸዋል።
የአውሮፓ ፓርላማ አባላት እንደሚሉት፧ በቻይና ሁኔታዎች መሠረታዊ ለውጥ ማሳየት ይጠበቅባቸዋል። በህዝባዊት ቻይና ሰብአዊ መብት አይከበርም። ከዚህም ሌላ፧ ከታይዋን ጋር ያለው ውዝግብ፧ እልባት አልተደረገለትም። ስለሆነም፧ በአሁኑ ወቅት ለቻይና ጦር መሣሪያ መሸጥ፧ ሊታሰብ እንኳ የማይገባው ጉዳይ ነው።