1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮፓው ኅብረት በኢራን ላይ የአገዳ ውሳኔ ማሳለፉ፣

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 20 2002

የአውሮፓው ኅብረት የውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች፣ ትናንት ባካሄዱት መደበኛ ስብሰባ በኢራን ላይ ጥብቅ እገዳ እንዲደረግ ውሳኔ አስተላልፈዋል።

https://p.dw.com/p/OVzi
ምስል AP

ያሁኑ እገዳ፤ በአገሪቱ የኃይል፣ የባንክና የገንዘብ ተቋማት እንዲሁም የንግድና የመገናኛ መሣሪያዎች ላይ ያነጣጠረ ሲሆን፤ ይህም ፤ ኢራን በምታካሂደው የኑክልየር መርኀ-ግብር ሳቢያ እንደሆn ነው የተገለጠው። አሜሪካም እንዲሁ ከአንድ ወር ገደማ በፊት በተመሳሳይ ምክንያት ጥብቅ እገዳ ማስተዋወቋ የሚታወስ ሲሆን፣ ካናዳም ፣ አውሮፓውያን እንዳደረጉት ሁሉ፣ በአገሪቱ የባንክና የኃይል ዘርፎች ላይ ያነጣጠረ እገዳ፣ ያስተዋወቀች መሆኑ ታውቋል። -- ገበያው ንጉሤ--

ተክሌ የኋላ

ሒሩት መለሰ