የአውሮፓ ህብረትና ሶሪያ
ማክሰኞ፣ ግንቦት 16 2003ማስታወቂያ
ህብረቱ በ 4 ህዝባቸውን ያሰቃያሉ በሚባሉ መንግሥታት ላይ ከጣላቸው ማዕቀቦች በተለይ መንግሥት ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን ተኩሶ በሚገድለት በሶሪያ ላይ ያሳለፈው የማዕቀብ ውሳኔ ከከዚህ ቀደሙ የተጠናከረ ነው ። አንዳንድ አስተያየት ሰጭዎች ማዕቀቡ ሥልጣን ላይ ላለው የሶሪያ መንግሥት አንዳንድ ምልክት ከመስጠት ውጭ መንግሥትን ለሚቃወሙ ወገኖች የሚፈይደው ነገር እንደማይኖር እየተናገሩ ነው ። የዛሬው አውሮፓ እና ጀርመን ዝግጅታችን የአውሮፓ ህብረት በተለይ በሶሪያ ላይ የጣለውን እገዳ ና ማዕቀብ ይመለከታል ።
ሂሩት መለሰ