1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮፓ ህብረት ሩስያ ና የሶሪያ ጦርነት

ረቡዕ፣ ግንቦት 28 2005

ትናንት ሩስያ ውስጥ በሶሪያ ጉዳይ ላይ ከሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር የተነጋገሩት የአውሮፓ ህብረት ፕሬዝዳንት ኽርማን ቫን ሮምፖይ « በጣም አስፈላጊ የፖለቲካ የሰላም ሂደት» ላሉት ለጄኔቩ ጉባኤ የአውሮፓ ህብረት ሙሉ ድጋፍ እንደሚሰጥ አስታውቀዋል ።

https://p.dw.com/p/18kHH
ምስል Reuters

ለሶሪያ ጦርነት መፍትሄ የሚሻ ጉባኤ ጄኔቫ ውስጥ እንዲካሄድ ሩስያና ዩናይትድ ስቴትስ ያቀረቡትን ሃሳብ እንደሚቀበል የአውሮፓ ህብረትም አስታውቋል ። የጄኔቩ ጉባኤ ሃሳብ አመንጪ ሩስያ በበኩሏ የሶሪያ ተቃዋሚዎች መከፋፈል ጉባኤው እንዳይሰምር አንዱ አደጋ ሊሆን እንደሚችል አሳስባለች ። በሌላ በኩል ፕሬዝዳንት ፑቲን  የአውሮፓ ህብረት በሶሪያ ላይ የጣለውን የጦር መሣሪያ ማዕቀብ ማራዘም ባለመቻሉ ማዘናቸውን ገልጸዋል ። የአውሮፓ ህብረትና ሩስያ ትናንት በሶሪያ ጉዳይ ላይ አትኩረው ስላካሄዱት ውይይት የብራሰልሱን ዘጋቢያችንን ገበያው ንጉሴን አነጋግሬዋለሁ ።

ገበያው ንጉሴ

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ