1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮፓ ህብረት አስተያየት በኢትዮዽያ ምርጫ ውጤት

ሐሙስ፣ ሰኔ 17 2002

4ኛው ዙር ሃገራዊ ምርጫን እንዲታዘቡ በኢትዮዽያ መንግስት በኩል ግብዣ ከተደረገላቸው ዓለም ዓቀፍ ተቋማት አንዱ የአውሮፓ ህብረት እንደነበረ ይታወሳል።

https://p.dw.com/p/O2V4
ምስል DW

የህብረቱ የምርጫ ታዛቢ ቡድን ባወጣው የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርቱ ምርጫው ዓለም ዓቀፍ መስፈርቶች የተጓደሉበት በጥቅልም ያላሟላ፤ እኩል የመወዳደሪያ ሜዳ ያልነበረው፤ ለገዢው ፓርቲ ባደላ መልኩ የተካሄደ እንደሆነ ገልጿል። የአውሮፓ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን የመጨረሻ ሪፖርት በእርግጥ ገና አልወጣም። በአንጻሩ ባለፈው ሰኞ የኢትዮዽያ ምርጫ ቦርድ የመጨረሻውን ውጤት ይፋ አድርጓል። የአውሮፓ ህብረት የኢትዮዽያ ምርጫ ቦርድን ይፋዊ ውጤት አስመልክቶ ምን ዓይነት አስተያየት ይሰጥ ይሆን? የብራስልሱ ወኪላችን ገበያው ንጉሴ የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሃላፊን ቃል አቀባይ አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ አሰናድቷል።

ገበያው ንጉሴ

መሳይ መኮንን

አርያም ተክሌ