1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮፓ ህብረት የስደተኞች አቀባበል መርህ

ዓርብ፣ ነሐሴ 3 2005

በትንሽቷ የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገር ማልታ የባህር ጠረፍ በሰዎች የተጨናነቁ ጀልባዎች ማረፊያ አጥተው ሁሌም ይጉላሉ ። በተደጋጋሚ በሜዲትራኒያን ባህር ላይ ጀልባዎች ይገለበጣሉ ፤ ይሰጥማሉ ሰዎችም ይሞታሉ ። ይሁንና በየቀኑ የአፍሪቃና የእስያ ስደተኞች ራሳቸውን ለአደጋ አጋልጠው በጀልባዎች ወደ ማልታ መምጣታቸው አልቆመም ።

https://p.dw.com/p/19N64
ምስል picture alliance/dpa

ሳብሪና ፓብስት እeደዘገበችው በሺህዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ማልታን ወደ መሳሰሉ ሃገራት የሚመጡት ከርስ በርስ ጦርነት ፣ ከድህነትና ከጭቆና በመሸሽና የተሻለ ህይወት ፍለጋም ነው ። ይሁንና ማልታን በመሳሰሉ የአውሮፓ ህብረት ድንበር ሃገራት ለብዙ ችግሮች ይጋለጣሉ ።
የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን በምህፃሩ UNHCR እንዳስታወቀው ባለፉት 6 ወራት ማልታና ኢጣልያ የባህር ጠረፎች የገቡት ስደተኞች ቁጥር 8400 ነው ። 415 ሺህ ነዋሪዎች ብቻ ላሏት ማልታ የስደተኞቹ ቁጥር እጅግ ከፍተኛ ነው ። የህብረቱ ድንበር የሆኑት ማልታን የመሳሰሉ ሃገራት በስደተኞች እየተጥለቀለቁ ነው ።

gekentertes Flüchtlingsboot Mittelmeer
በሜዴትራንያን ባህር ልትስጠም የነበረች ስደተኞች የጫነች ጀልባምስል picture-alliance/dpa

እነዚህ ስደተኞችም በማልታ ለተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ይጋለጣሉ ። ፕሮ አዝዩል የተባለው በአውሮፓ ተገን ማግኘት ለሚፈልጉ ስደተኞች መብት የሚቆመው ድርጅት ቃል አቀባይ ካርል ኮፕ ስደተኞቹ ማልታን ወደ መሳሰሉ ሃገራት በብዛት ቢጎርፉም መንግሥታት የሰብዓዊ መብታቸው መጣስ እንደሌለበት ያሳስባሉ ። « የአውሮፓ ህብረት ድንበር የሆኑት ሃገራት በከፊል በስደተኞች ተጨናንቀዋል ። ሆኖም ሃገራቱ በስደተኞች መጨናነቃቸው በምንም ዓይነት በነዚህ ሃገሮች ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ክፉኛ እንዲጣስ ሰበብ ሊሆን አይገባም ። »ግሪክም ስደተኞች በብዛት ከሚጎርፉባቸው አገሮች አንዷ ናት ። ህገ ወጥ የሚባሉ ስደተኞች ወደ ግሪክ የሚመጡት በባህር ብቻ ሳይሆን በቱርክ በኩል በየብስም ጭምር ነው ። እንደ ማልታ ሁሉ የግሪክ የስደተኞች መጠለያዎችም ተጨናንቀዋል ። የአውሮፓ ድንበር ወደ ሆኑት ሃገራት የሚመጡ ስደተኖች ከወዲህ ወዲያ እንደሚለጋ ኳስ ከሃገር ሃገር እንዲከራተቱ ይደረጋል ። ለምሳሌ በመጀመሪያ ኢጣልያ የደረሱ ስደተኞች እዚያ የተገን ማመልከቻ አስገብተው ወደ ሌላ

Afrikanische Migranten Immigranten illegale Einwanderer Italien
አፍሪቃውያን ስደተኞች በኢጣልያምስል AP

የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገር ቢሄዱ መጀመሪያ ወዳመለከቱበት ሃገር መልሰው ይልኳቸዋል ። ስደተኞቹ እንደምንም ብለው ጀርመን ኔዘርላንድ ወይም ስዊድን ቢገቡ ተመልሰው ወደ ሜዴትራኒያን ባህር አዋሳኝ ሀገሮች የመባረር እጣ ሊገጥማቸው ይችላል ። ጀርመን በአሁኑ ጊዜ በግሪክ በኩል የመጡ ስደተኞችን መልሳ ወደ መጡበት አትልክም ። የጋራው የአውሮፓ የስደተኞች አቀባበልና አያያዝ መርህ ከሰኔ መጀመሪያ አንስቶ ተግባራዊ ሆኗል ።የአውሮፓ ህብረት ከዚያ በፊት በነበረው አቋም የስደተኞች ጉዳይ በተናጠል መታየት ያለበት ጉዳይ አድርጎ ነበር የሚወስደው ። ተገን ጠያቂዎችን የሚመለከተው ፖለቲካ አሁን በመላው አውሮፓ በህግ እልባት ሊደረግለት ይገባል ይላሉ አክስል ፎስ በአውሮፓ ፓርላማ የወግ አጥባቂው የCDU ተወካይ

Lampedusa Migration
ስደተኖች በለምፔዱዛምስል picture-alliance/dpa

« አሁን ያለው ሁኔታ የእያንዳዱ ሃገር በተናጠል ሳይሆን በጋራ የሚወጣው ጉዳይ ነው ።
በአረቡ ዓለም ህዝባዊ ንቅናቄ በአንድ ጊዜ ብዙ ስደተኞች ወደ አውሮፓ ህብረት መምጣታቸው በግልፅ ታይቷል ። በዚህም አባል ሃገራትን ስደተኞችን ተቀብሎ በማስተናገድ ረገድ ከአቅም በላይ ሆኖ ታይቷል ። »

ስለዚህ ፎስ የጋራ የሆነ መፍትሄ መገኘት አለበት ሲሉ ሃሳብ ያቀርባሉ ። ይህም ሲባል ታዲያ ሰዎች በተለይ በጦርነት ሳቢያ ከትውልድ ሃገራቸው የሚፈናቀሉትን ሆኖም ጦርነቱ ካለቀ በኋላ መመለስ የሚሹትን ነው ። ካርል ኮፕ ግን ህብረቱ የተሳሳተ ቀውስ የማስወገጃ መንገድ እየተከተለ ነው ሲሉ ነቅፈዋል ።
« ብዙ ሰዎችን ከማፈስና አዳዲስ ማጎሪያ ጣቢያዎችን በአውሮፓውያን ገንዘብ ከመገንባት ይልቅ ሰብዓዊ ክብርን በሚጠብቅ መልኩ ግሪክ ውስጥ መጠለያ ጣቢያዎችን በገንዘብ መደገፍ በተቻለ ነበር ። ከዚህም ጋር ተያይዞ ህዝቦቻቸውን አፍነው የሚይዙ መንግሥታትን ማስወገድ በተቻለ ነበር ። »

ሂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሰ