1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮፓ ሕብረት የሶሪያ ማዕቀቡን አስፋፋ

ቅዳሜ፣ ነሐሴ 28 2003

መንግሥት የሕዝቡን እንቅስቃሴ ለመቅጨት የጭካኔ ዕርምጃ መውሰድ በቀጠለባት በሶሪያ የተፋጠነ የመንግሥት ለውጥ ይደረግ ዘንድ ፈረንሣይ ጥሪ አደረገች።

https://p.dw.com/p/Rjkw
ምስል picture alliance/dpa

ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አላን ዡፔ ለዚሁ ዓላማ በሶሪያው ፕሬዚደንት በባሸር-አል-አሣድ ላይ የሚደረገው ዓለምአቀፍ ግፊት ይበልጥ መጠናከር እንዳለበት በዛሬው ዕለት አስገንዝበዋል። የአውሮፓ ሕብረት መፍቀረ-ዴሞክራሲውን እንቅስቃሴ ለማፈን ዓመጽን መጠቀም በቀጠለችው በሶሪያ ላይ ማዕቀቡን ለማስፋፋት ትናንት መስማማቱ አይዘነጋም። አዲሱ ማዕቀብ ከሶሪያ ነዳጅ ዘይት ማስገባትን፤ እንዲሁም ከሶሥት የሶሪያ ኩባንያዎችና አራት የንግድ ግለሰቦች ጋር አብሮ መስራትን በአውሮፓ ደረጃ የሚያግድ ነው። ማዕቀቡ ከፊታችን ሕዳር ወር የመጀመሪያ ሣምንት ጀምሮ እንደሚጸና ይጠበቃል። ሶሪያ ውስጥ በቀጠለው መንግሥታዊ ዓመጽ በትናንትናው እለትም በአገር-አቀፍ ደረጃ ቢያንስ 17 ተቃዋሚዎች ተገድለዋል።

መስፍን መኮንን

አዜብ ታደሰ