1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮፓ የስደተኞች አቀባበል መርህ

ሐሙስ፣ መስከረም 25 2004

ካለፉት 6 ወራት ወዲህ በሰሜን አፍሪቃ በተቀጣጠሉት ህዝባዊ ንቅናቄዎች ምክንያት በየሃገሩ መውጫ አጥተው የሚሰቃዩ እንዲሁም ህይወታቸውን ለአደጋ አጋልጠው ማልታና ግሪክ ደርሰው በስደተኞች ማጎሪያዎች የሚንገላቱ ስደተኞች ቁጥር ከፍተኛ ነው ።

https://p.dw.com/p/RpV2
ስድተኞች በግሪክምስል picture alliance/dpa

ቀድሞም በስደተኞች የተጨናነቁት ግሪክ ና ማልታ ከአረቡ ዓለም ህዝባዊ አብዮት በኋላ የሚጎርፈውን ስደተኛ የያዙበት መንገድ አሳዛኝ መሆኑን ስደተኞችም ሆነ አካባቢውን የጎበኙ የአውሮፓ ፖለቲከተኞች ጭምር የሚናገሩት ነው ። በዚህ ዓይነት ሁኔታ የሚሰቃዩትን ስደተኞች የተቀሩት የአውሮፓ ህብረት አባል ሃገራት እንዲያስጠጉ በተደጋጋሚ ቢጠየቁም እስካሁን አጥጋቢ መልሰ አልሰጡም ። የችግሩን አሳሳቢነት በማጉላት ለአውሮፓ መንግሥታት ተጨማሪ ጥሪ ያስተላለፈ ስብሰባ ትናንት ብራሰልስ ቤልጂግ በአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ተካሂዷል ። ስብሰባውን የተከታተለውን የብራሰልሱ ዘጋቢያችን ገበያው ንጉሴን ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግሬዋለሁ ።

ሂሩት መለሰ

ገበያው ንጉሴ

አርያም ተክሌ