1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮፓ የስደተኞች ፖሊሲና የኤርትራ ስደተኞች

ሰኞ፣ ኅዳር 27 2008

በኤርትራ ስደተኞች ላይ አንዳንድ አገሮች እሉታዊ አመለካከት ማሳየት መጀመራቸው የህብረቱ አባላት የስደተኖች ፖሊሲ ለውጥ ማሳያ ነው እየተባለ ነው። ህብረቱ ከኤርትራ መንግስት ጋር በመሥራት የስደተኖችን ቁጥር ለመቀነስ ፍላጎት አለው፣ በቫሌታው ስምምነት ለስደተኞች ከተመደበው 1.8 ቢሊዮን ዩሮ፣ ኤርትራ ተጠቃሚ እንደምትሆን ተገልጿል።

https://p.dw.com/p/1HIkT
Frankreich Flüchtlinge Eurotunnel Calais
ምስል Getty Images/AFP/P. Huguen


ወደ አውሮፓ በብዛት የሚገቡትን ስደተኖች ቁጥር ለመቀነስ፣ የህብረቱ አባል አገሮች ያተኮሩት ለስደት በሚዳርጉ መረታዊ ችግሮች ዙሪያ ሳይሆን፣ ሰዎች ወደ ክፍለ ዓለሙ እንዳይገቡ ለማድረግ በሚያስችሉ የመከላከያ ዘዴዎች ላይ እንደሆነ እየተገለጸ ነው። በቅርቡ የተደረገው የቫሌታ ማልታው ጉባኤም ሆነ ከቱርክ ጋር የተደረሰው ስምምነት፣ ሰዎች እንዳይሰደዱ ለማድረግ የሚረዱ፣ ከተሰደዱም በኋላ ተገቢውን እንክብካቤ እንዲያገኙ ለማድረግ በሚያስችሉ መርሃ ግብሮች ላይ ትኩረት የሚያደርጉ አይደሉም በማለት የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ይወቅሳሉ። በኤርትራ ስደተኞች ላይ አንዳንድ አገሮች እሉታዊ አመለካከት ማሳየት መጀመራቸው የህብረቱ አባላት የስደተኖች ፖሊሲ ለውጥ ማሳያ ነው እየተባለ ነው። ህብረቱ ከኤርትራ መንግስት ጋር በመሥራት የስደተኖችን ቁጥር ለመቀነስ ፍላጎት እንዳለው የተገለጸ ሲሆን፣ በቫሌታው ስምምነት መሰረትም፣ ለስደተኞች መርጃ ከተመደበው አንድ ነጥብ ስምንት ቢሊዮን ዩሮ፣ ኤርትራ ተጠቃሚ እንደምትሆን ተገልጿል። የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ግን የኤርትራ ወጣቶችን ለስደት የሚዳርገው ብሄራዊ ውትድራና ገደብ ሳይበጅለት ከኤርትራ መንግስት ጋር ለመሥራት መወሰኑ ትክክል አይደለም በማለት ይከራከራሉ ።የዛሬው ማህደረ ዜና ፕሮግራም የህብረቱን የስደተኞች ፖሊሲና የኤርትራ ስደተኖችን እጣ ፈንታ ይምረምራል።

ገበያዉ ንጉሴ

ሂሩት መለሠ