1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአየርላንድ ግድያና የብሪታንያ ይቅርታ

ረቡዕ፣ ሰኔ 9 2002

የዛሬ 38ዓመት ለተገደሉ 13 ሰልፈኞች ብሪታኒያ ይቅርታ ጠየቀች

https://p.dw.com/p/NsXv
ጥቁሩ እሁድምስል AP

የብሪታንያ ወታደሮች በ1964 በአየርላንድ ሠላማዊ ሠልፈኞች ላይ ተኩስ ከፍተዉ ላጠፉት ሕይወት የብሪታንያ ጠቅላይ ሚንስትር ዴቪድ ኬሜሩን ትናንት በይፋ ይቅርታ ጠየቁ።«ጥቁሩ-እሁድ» ተብሎ በሚጠራዉ ዕለት የብሪታንያን አገዛዝ በመቃወም አደባባይ ከወጡ ሠላማዊ ሠልፈኞች መካካል አስራ-ሰወስት ሰዎች ተገድለዉ ነበር።ግድያዉ እቅከ ቅርብ ጊዜ ድረስ እንዳነጋገረ ነዉ።ግድያዉንና ምክንያቱን እንዲያጣራ የቀድሞዉ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚንስትር ቶኒ ብሌር የሰየሙት ኮሚሽን አስራ-ሁለት አመታት የፈጀ የምርመራ ዉጤቱን ትናንት ይፋ አድርጓል።በምርመራዉ ዉጤት መሠረት ወታደሮቹ ንፁሐን ሰዎችን ነዉ-የገደሉት።ያሁኑ ጠቅላይ ሚንስትር ዴቪድ ካሜሩን ለደረሰዉ ጥፋት ይቅርታ ጠይቀዋል።መሳይ መኮንን ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።

መሳይ መኮንን

ሂሩት መለሰ