1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአየር ንብረት ለዉጥ ተመልካች ጉባኤ በፓሪስ

ሰኞ፣ ኅዳር 20 2008

ዓመታዊዉ የተመድ የአየር ንብረት ለዉጥ ተመልካች ጉባኤ ፓሪስ ፈረንሳይ ላይ ዛሬ ተጀምሯል። ጉባኤዉ ባለፉት ዓመታት ሲካሄዱ የቆዩ ድርድርና የመስማሚያ ነጥቦችን መነሻ አድርጎ የሚነጋገር ሲሆን ለሁለት ሳምንት ይቆያል።

https://p.dw.com/p/1HEfH
Frankreich Klimagipfel in Paris Merkel und Obama
ምስል Reuters/K. Lamarque

[No title]

በጉባኤዉ 150 ሃገራትን የሚወክሉ የሀገር መሪዎች፣ የአካባቢ ተፈጥሮ ጥበቃ ሚኒስትሮች፣ የአካባቢ ተፈጥሮ ጉዳይ ተመራማሪዎች እና ተሟጋቾች እንዲሁም በዘርፉ ላይ የሚሠሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ይሳተፋሉ። የዓለም የሙቀት መጠን ከሁለት ዲግሪ እንዳይበልጥ የሚለዉ የብዙዎቹ ሃገራት ሃሳብ ቢሆንም አፍሪቃ እና የደሴት ሃገራት ከሁለት ዲግሪ በታች ዝቅ እንዲል ነዉ የሚጠይቁት። የአየር ንብረት ለዉጥ እና የከባቢ አየር ብክለት ተጠቂ የሆኑ ሃገራት ከችግሩ ጋር ተላምደዉ ሊኖሩ እንዲችሉ ለብክለቱ ታሪካዊ ተጠያቂነት ያላቸዉ በኢንዱስትሪ የበለፀጉ ሃገራት ሊያዋጡት ቃል የገቡት የመቶ ሚሊየን ዶላር ጉዳይም ሌላዉ እልባት ያላገኘ አነጋጋሪ ጉዳይ ነዉ። ሸዋዬ ለገሠ ከፓሪሱ የአየር ንብረት ለዉጥ ተመልካች ጉባኤ ምን ይጠበቃል ስትል ኢትዮጵያዊ የአካባቢ ተፈጥሮ ተሟጋችን በአጭሩ አነጋግራለች።

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ