1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአየር ንብረት ለዉጥ ጉባኤ በቦን

ማክሰኞ፣ ሰኔ 7 2003

በአዉሮጳዉያኑ 1997ዓ,ም በታህሳስ ወር ጃፓን ኪዮቶ ላይ የጸደቀዉ የበካይ ጋዞች ቅነሳ ዉል የሚያበቃበት የጊዜ ገደቡ ተቃርቧል፤ 2012።

https://p.dw.com/p/RTQs
ክርስቲና ፊጉርስምስል DW

ዉሉን በሌላ ለመተካት ድርድሮች በየደረጃዉ ይካሄዳሉ። ካለፈዉ ሳምንት ሰኞ አንስቶ በጀርመን ቦን ከተማ በ184 ሀገራት መካከል በዚህ ረገድ የሚካሄደዉ ድርድር ከተስፋዉ ቀቢጸ ተስፋዉ ልቆ መታየቱ ነዉ የሚነገረዉ። ጉባኤዉ የፊታችን ዓርብ ሰኔ 10 ቀን 2003ዓ,ም ይጠናቀቃል። ቀጣዩ ድርድር ጃፓን ላይ በሐምሌ ወር ይደረጋል። የዘንድሮዉ የተመድ ዓመታዊ የአየር ንብረት ለዉጥ ጉዳይ ጉባኤ በሚቀጥለዉ ዓመት ከህዳር ወር መገባደጃ አንስቶ በደቡብ አፍሪቃ ደርባን ከተማ ይካሄዳል።

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ