የአየር ንብረት ቀውስና -የዝናም እጦት፣
ረቡዕ፣ ጥቅምት 25 2002ማስታወቂያ
ውጤቱ ታዲያ በዝናም ብቻ የሚመካን ግብርና፣ መቅኖ የሚያሳጣና ህዝብን ለረሃብ የሚዳርግ ነው የሚሆነው። በመሠረቱ ብዙ ወንዞች በሚፈሱባት አገር ፣ በአንዳንድ ወቅቶች ዝናም በመጥፋቱ ብቻ ህዝብ፣ በምንም ዓይነት ተርቦ ለእልቂት ሊዳረግ ባልተገባው ነበር። በመርኅ ደረጃ፣ አማራጭና ዘላቂ መፍትኄዎችን መሻት የግድ ይላልና! ያም ሆኖ ፣ በአየር ንብረት ላይ ፣ ቀውስ የሚያስከትሉ ሁኔታዎች መከሠታቸው በየአህጉሩ ባለሙያዎችን ማነጋገሩን እንደቀጠለ ነው። በዛሬው ሳይንስና ኅብረተሰብ ቅንብራችን ፣ ከጥቅምት 11-13 ,2002 ዓ,ም ፣ ቦን ውስጥ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አካሂዶት በነበረው፣ በአየር ንብረት ቀውስና በመከላከያ እርምጃዎች ላይ ባጤነ ጉባዔ ተሳትፈው ከነበሩ አንድ ኢትዮጵያዊ የዘርፉ ባለሙያ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ እናሰማለን።
ተክሌ የኋላ/ነጋሽ መሐመድ